የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች እና የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች /Stationaries/ እቃዎች ግዥ ለማከናወን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU-PPM/01/2019 (NCB)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች እና የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች /Stationaries/ እቃዎች ግዥ ለማከናወን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታ መወዳደር ይችላሉ፡፡
| ሎት | የተለያዩ እቃዎች | የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን | ጨረታው የሚዘጋበት ቀን ቀንና ሰዓት | ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት |
| 1 | የተለያዩ የጽዳት እቃዎች | 50,000.00 | መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት | መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም 8:30 ሰዓት |
| 2 | የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች /Stationaries | 75,000.00 | መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት | መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም 8:30 ሰዓት |
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ነሐሴ 30 ቀን 2018 ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል የኢ.ኤ.አ ፕሮጀክቶች ፖርትፖልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራ መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል ከኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1101 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በተገለጸው የብር መጠን መሰረት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለውን የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢ.ኤ.አ. አ.አ.ኤ.አ.ፕ ወይም EEU-UEAP ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU-PPM/01/2019 (NCB) የሚል ምልክት በማድረግ እና ከላይ በተራ ቁጥር-2 በተገለጸው አድራሻ እስከ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ መስከረም 12 ቀን 2019 ከቀኑ 8፡30 ላይ ይከፈታል።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጧት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት 7፡00-11፡00 እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00 -- 6፡00 ሰዓት መመልከት ይችላሉ፡፡
- የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0111263159 መደወል ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
