Tender Detail

Tender Details

  • Company የራያ ቆቦ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
  • Address በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0912376341
  • Website
  • Deadline30 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 500 /አምስት መቶ ብር/
  • Bid Security5000 /አምስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፕኦ/
  • opening dateበ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Disposal Sale , Vehicle

Sale of used vehicles and motorcycles

የራያ ቆቦ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የራያ ቆቦ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ያገለገሉ መኪኖች እና ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም

*        በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያለው፤

*        የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ መያያዝ አለበት፤

*        የዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፤

*        የጨረታ ሰነዱ ራያ ቆቦ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ብር 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ መግዛት ይቻላል፤

*        ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 5000 /አምስት ሺህ ብር / በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፕኦ/ በመ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ፖስታው ውስጥ አሽጎ /አያይዞ/ ማቅረብ ይኖርበታል፤

*        የጨረታ ሰነዱን ኦርጂናልና ኮፒ በማድረግ በሁለት በተለያየ ፖስታ በማዘጋጀት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል፤

*        በአሸናፊው ተጫራች ላይ ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም፤

*        የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ባቀረቡት መወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፤

*        ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ሰነዱን ራያ ቆቦ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 25 የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መውሰድ ይቻላል፤

*        ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤

*        የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖረው በጥንቃቄ መሞላት አለበት፤

*        ጨረታው የሚከፈተው ቅዳሜና እሁድ ወይም መንግስት ካላንደር የሚዘጋው ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።

*        መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

*        ለበለጠ መረጃ በመስሪያ ቤቱ የስልክ ቁጥር 09 12 37 63 41፤ 09 16 92 66 84 ወይም 09 12 31 94 06 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።

የራያ ቆቦ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for the sale of used vehicles and motorcycles by Raya Kobo District Finance and Economic Cooperation Office. Bidders must hold a renewed trade license and TIN number. Detailed specifications are available in the tender document.
Save Tender