Tender Detail

Tender Details

  • Company የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ነጆ ከተማ : በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 09 17 09 37 49
  • Website
  • Deadline03 Sep 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለያንዳንዱ ሰነድ
  • Bid Securityሎት 1/20,000 ብር፤ ሎት 2/20,000 ብር፤ ሎት 3/25,000 ብር፤ ሎት 4/20,000 ብር፤ ሎት 5/25,000 ተመላሽ የሚሆን ብር የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ
  • opening dateበ4፡30 ነሐሴ 28/12/18
  • Categories Cleaning & Janitorial , Electrical And Electromechanical , Office Supplies And Services

የጽህፈትና የጽዳት መሣሪያዎች፣ የደንብ ልብስ መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፣ የግንባታ ዕቃና የመኪና ጎማ መሣሪያዎች ግዥ

የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደር አገልግሎት የሚውሉ፤ ሎት 1. የጽህፈትና የጽዳት መሣሪያዎችን፤ ሎት 2. የደንብ ልብስ መሣሪያዎች፤ ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፤ ሎት 4. የግንባታ ዕቃና ሎት 5. የመኪና ጎማ መሣሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፤

  1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር የተዛመደ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የ2018 ግብር የከፈሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር መረቀት ያላቸው፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
  5. ጽ/ቤታችን የሚገዛቸውን ዕቃዎች እንዳስፈላጊነቱ በቀረበው አንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ብዛቱን ማዘዝ ይችላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለያንዳንዱ ሰነድ በመከፈል ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ቀርበው መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመለየት በፖስታ ከታሸጉ በኋላ ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ በነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  8. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ዕቃውን ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማቅረብ በባለሙያ ታይቶ ርክክብ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
  9. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፍኬሽን መሰረት ካልቀረቡና ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈጠር ሃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል፡፡
  10. የዕቃዎቹ ዋጋ የሚከፈለው ዕቃዎቹ ግምጃ ቤታችን ገቢ ከሆኑ በኋላ ነው፡፡
  11. ጨረታው ከነሐሴ 7/12/18 እስከ ነሐሴ 28/12/18 ቆይቶ ጨረታው ሣጥን ይዘጋል፡፡ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 የሚከፈት ሲሆን፣ ተጫራቾች ቢገኙም በይገኙም ጨረታውን አያስተጓጉልም፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሎት 1/20,000 ብር፤ ሎት 2/20,000 ብር፤ ሎት 3/25,000 ብር፤ ሎት 4/20,000 ብር፤ ሎት 5/25,000 ተመላሽ የሚሆን ብር የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  13. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ ይኖርበታል፡፡
  14. ማንኛውም ተጫራች ለሚያቀርበው መሣሪያ ብራንድና ማርኩን ግልጽ አደርጎ በሰነድ አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
  15. እንደ አስፈላጊነቱ ከተጫራቾቹ አሸናፊ የሆኑ ጋር የውል ስምምነት እስከ መጋቢት 30/2019 ሊቆይ ይችላል፡፡
  16. በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች ለውጪ ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  17. በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች የጨረታውን ግዴታ ባይመጣ ለውል ማስከበሪያ 10% ያስያዘው ገንዘብ ለጽ/ቤት ገቢ ይሆናል፡፡
  18. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች ለደንብ ልብስ ጨረታ የሚያቀርቡትን ዕቃዎች ናሙና⁄ Sample የማቅረብ ግዴታ አለበት፤ በተጨማሪም የሚቀርበው ናሙና የተጠየቀ ብቻ መሆን አለበት፡፡
  19. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 0917093749 / 0922429665, 0917299570

የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Procurement of office, cleaning, clothing, electronics, construction materials, and vehicle tires across five lots for city administration use. Bidders need valid trade licenses, tax compliance, VAT registration, and supplier registration. Delivery to city warehouse; samples required for clothing lot.
Save Tender