የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የህንፃ መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የደምብ ልብሶች ግዥ
በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጅማ ገነቲ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጅማ ገነቲ ወረዳ ገንዘብ/ቤት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን፤ አላቂ የቢሮ እቃዎችን፤ ቋሚ እቃዎችን፤ የህንፃ መሳሪያዎችን፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ና የደምብ ልብሶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ፡-
- በዚህ ስራ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ገንዘብ ቤት የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና ተጫራች እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ሰነድ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ገ/ቤት በጅማ ገነቲ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር.2 የማይመለስ ብር 1000(አንድ ሺህ) ከፍለው ጨረታው ከወጣበት ቀን ነሐሴ 7/12/2018 ዓ.ም ተከታታይ 15 የስራ ቀናት መካከል በየቀኑ ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ 500,000/አምስት መቶ ሺህ/ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
- የሚያቀርቡትን የዋጋ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን 7/12/ 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 28/12/18 ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በጅማ ገነቲ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ነሐሴ 28/12/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 በጅማ ገነቲ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በራሳቸው ወጪ እቃውን የሚያቀርቡት በጅማ ገነቲ ወረዳ ሐረቶ ከተማ ገ/ኢ/ል/ት/ቤት ድረስ ይሆናል።
- በሰነዱ ላይ የተጠቀሰው የእቃው ብዛት (Quantity) 20% ለመቀነስም ሆነ ለመጨመር መስሪያ ቤቱ ሙሉ መብት አለው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-10 42 09 29, 09-20 41 51 63, 09 11 59 93 93 በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጅማ ገነቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of various office supplies, furniture, fixed assets, building equipment, electronics, and uniforms by Jimma Geneti District Finance Office. Bidders must hold a valid trade license, tax clearance, and VAT registration. Delivery is to Haretu Town district office.
