የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች፣ የተለያዩ የህትመት ውጤቶች፣ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ የተማሪዎች ካርድ ህትመቶች፣ የደንብ ልብስ፣ የሞተር ሳይክል ግዥ፣ የመኪናና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ
የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች፣ የተለያዩ የህትመት ውጤቶች፣ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ የተማሪዎች ካርድ ህትመቶች፣ የደንብ ልብስ፣ የሞተር ሳይክል ግዥ፣ የመኪናና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለይ ለመወዳደር ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- 2019 ዓ.ም. ግብር የገበረና የንግድ ፈቃዱን ያደሰ፡፡
- ቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፒኦ (CPO) ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ለመፈራረም ፍቃደኛ የሆነ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር ለወረዳ ገቢዎች በመከፈል ከግዥ ክፍል መግዛት የሚችል፡፡
- Withholding Tax (3%) ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ፡፡
- በማይክሮ የተደራጁ ካደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከአንድ ጊዜ በላይ ለውድድር የቀረቡ 2% ሲፒኦ ማስያዝ ይገደዳሉ፡፡
- በደንብ ልብስ አቅርቦት ላይ ለሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የጨርቁን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዳቸውን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለይቶ በማሽን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሌሎች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ በህግ የተከለከለ ነው፡፡
- የመመዝገቢያ ቦታ ጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ይሆናል፡፡
- የመመዝገቢያ ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ2 ቀን በኋላ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች አየር ላይ ይቆያል፡፡ ጨረታው የሚዘጋው በ15ኛው ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቹ ባሉበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ሊከፈት ይችላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን እቃ በራሱ ወጭ እስከ ጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ድረስ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የእቃው ብዛት በ20% ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
➢ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 047-342-03-03
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጅማ ዞን የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Gera District Finance Office seeks open tender to procure office supplies, equipment, electronics, tires, print products, student cards, uniforms, motorcycles, and spare parts. Bidders must have valid trade license, tax clearance, VAT registration, and submit uniform samples.
