Tender Detail

Tender Details

  • Company የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የባቢሴ ከተማ አስተዳደርገንዘብ ጽሕፈት ቤት
  • Address Oromia Ethiopia, Phone: ቁጥር: 0921845053 / 0914947011
  • Website
  • Deadline26 Aug 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 1,000 (አንድ ሺህ) (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) (በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO))
  • opening dateባሉት 15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Electrical And Electromechanical , Office Supplies And Services

የባቢሌ ከተማ አስተዳደር የገንዘብ ጽሕፈት ቤት የ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ

የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የባቢሴ ከተማ አስተዳደርገንዘብ ጽሕፈት ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በአሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የባቢሌ ከተማ አስተዳደር የገንዘብ ጽሕፈት ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለሁሉም የመንግሥት ጽሕፈት ቤቶች እና የከተማው ቀበሌዎች የሚሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሚገዙ ዕቃዎች

  • ደንብ ልብስ
  • የጽዳት ዕቃዎች
  • የጽሕፈት መሣሪያዎች (Stationery)
  • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • የፈርኒቸር ዕቃዎች
  • ለቴክኒከና ሙያ ኮሌጅ ሥልጠና የሚሆኑ ዕቃዎች
  • የተሸከርካሪና የሞተር ብስከሌት መለዋወጫዎች

የጨረታ መስፈርቶች

  1. ተወዳዳሪዎች የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የፋርኒቸርና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የሚገልጽ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
  2. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት (Supplier Registration Certificate) ማቅረብ አለባቸው።
  3. ከገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ የግብር ክሊራንስ (Tax Clearance) ማቅረብ አለባቸው።
  4. የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተወዳዳሪዎች በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ለጠቅላላው ሰነድ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተወዳዳሪዎች ዕቃዎቹን የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ) በመከፈል ከባቢሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽሕፈት ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተወዳዳሪዎች የተወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውን (Original) እና ፎቶ ኮፒውን በመለየትና በሰም በማሸግ በባቢሌ ከተማ ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዕቃ በገባው ውል መሠረት በራሱ ትራንስፖርት እስከ ባቢሌ ከተማ ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት።
  9. ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በማስታወቂያው ላይ የተጠቀሱትን፡ የኮምፒውተር እስክሪብቶ፣ የኮምፒውተር ወረቀት፣ የፎቶ ኮፒ እስከሪብቶ፣ የሥራ ልብስ እና ለሴት ሠራተኞች የሚሰጥ ጫማ አንድ አንድ ናሙና (Sample) ማቅረብ አለባቸው።
  10. የጨረታ ሰነዱ የተሰረዘና ስህተት ያለበት ከሆነ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
  11. የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  12. ተወዳዳሪዎች በሰነዱ ገጾች ሁሉ ላይ ማኅተምና ፊርማ ማድረግ አለባቸው።
  13. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት ዕቃ በሀገር ውስጥ የጥራት ደረጃ የተረጋገጠ መሆን አለበት።
  14. ተወዳዳሪው ከዚህ ቀደም በመንግሥት ግዥዎች እንዳይሳተፍ ያልተከለከለ መሆኑን የሚያስረዳ መረጃ ከመንግሥት ንብረት ማስወገድና ግዥ ኤጀንሲ ማቅረብ ወይም በዌብሳይት የተረጋገጠ መሆን አለበት።
  15. ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  16. ጽሕፈት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ:- በስልክ ቁጥር: 0921845053 / 0914947011 በሥራ ሰዓት ይደውሉ።

የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የባቢሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽሕፈት ቤት

✨ messages.ai_summary
Babile City Administration Finance Office seeks bids for uniforms, cleaning supplies, stationery, electronics, furniture, TVET training materials, and vehicle/motorcycle spare parts for government offices and kebeles. Bidders need valid trade license, supplier registration, tax clearance, VAT certificate, and no prior debarment. Goods must meet national quality standards; delivery to Babile at bidder’s transport.
Save Tender