Tender Detail

Tender Details


procurement of veterinary equipment


Source: World Bank — Livestock and Fisheries Sector Development Project

                                                         የእንስሳት ህክምና መገልገያ መሳሪያዎች የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

                                                                       የግዥው መለያ ቁጥር ET-AMH-LFSDP-GO-RFQ-05/2011

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ፕሮጀክቱ ለሚደግፋቸው ወረዳዎች የእንስሳት ክሊኒክ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እንስሳት ጤና ህክምና መገልገያ መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግዥው መጠን ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሊ፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከፋይናንሻል ፕሮፖዛል ከኦሪጅናል ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 (ሀምሳ ብር) በመክፈል አብክመ ግብርና ቢሮ ቢሮ ቁጥር 71 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፐ.ኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን የቴክኒክ ዶክመንትና የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ዶክመንት) ዋናና ቅጅ በማለት በፖስታ አሽጎ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት  ቀን ጀምሮ ማቅረብ ይችላል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ታህሳስ  30 ቀን 2011 ዓ.ም 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583205297 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

                                                                                                                                                                     የአብክመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት

                                                                                                                                                                                                                  ባህር-ዳር

Save Tender