የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ፣ የውሃ እቃዎችና መገጣጠሚያ፣ የተሽከርካሪ ጎማና መለዋወጫ እቃዎች፣ የእንስሳት መድሀኒትና መገልገያ፣ ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ደብ ልብስ፣ ቋሚ እቃዎችና መሰል (ፈሪኒቸር ውጤቶች)፣ ኬሚካል አፓራተስ ግዥ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው አገልግሎት የውሉ ሎት፡ የጽህፈት መሳሪያ፤ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ፣ ሎት 5 የውሃ እቃዎችና መገጣጠሚያ፤ ሎት 6 የተሽከርካሪ ጎማና መለዋወጫ እቃዎች፤ ሎት 7 የእንስሳት መድሀኒትና መገልገያ፣ ሎት 8 ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ሎት 9 ደብ ልብስ፣ ሎት 10 ቋሚ እቃዎችና መሰል (ፈሪኒቸር ውጤቶች)፡ ሎት 11 ኬሚካል አፓራተስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነበር) ያላቸው
- የድርጅት ህጋዊ ማህተም ያለው (ያላት)
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 ብር (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል (የምትችል)
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለጽህፈት መሳሪያ 35000 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር)፤ ለኤሌክትሮኒክስ 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር)፣ ለጽዳት እቃዎች 6000 ብር (ስድስት ሺህ ብር)፤ ደብ ልብስ 30,000 ብር (ሰላሳ ሺህ ብር) ለስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ 25,000 ብር (ሀያ አምስት ሺህ ብር)፤ ለቋሚ አላቂ እቃዎች 15,000 ብር (አስራ አምስት ሺህ)፤ ለውሃ እቃና መገጣጠሚያ እቃዎች 30,000 ብር (ሰላሳ ሺህ)፤ ለተሽከርካሪ ጎማና መለዋወጫ 16000 ብር (አስራ ስድስት ሺህ)፤ ለእንስሳት መድሀኒትና መገልገያ ቋሚ አላቂ እቃዎች 10,000 ብር (አስር ሺህ)፣ ለኬሚካል አፓራተስ 10,000 ብር (አስር ሺህ)፤ ለቋሚ እቃዎችና መሰል 60,000 ብር (ስልሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ወይም ከሚታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲ/ፒ/ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታ ዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፓስታ ኢንቮልቭ በማደረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 (አራት ሰዓት) ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል። ጨረታው በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 (አራት ሰዓት ተኩል) ላይ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።
- የእቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ። የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 ብር (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል (መሉ በሙሉ) ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሄራዊ በዓላት ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑ ይታወቃል።
- የጨረታው ተሳታፊዎች ፓስታ ላይም ሆነ ዋጋ መሙያው ላይ ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው።
- የጨረታ ጸንቶ መቆያ ጊዜው 45 ቀን መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች ካሁን በፊት ተጫርተው ህጋዊ እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን አለባቸው። ለዚህም ማረጋገጫ ከሰሩበት ወይም ካሁን በፊት ካቀረቡበት ተቋም የመልካም ስራ አፈፃፅም ማምጣት ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን - ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ቢሮ ቁጥር 3 በአካል ለበመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0111190280 ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- ከአ/አባ በስተሰሜን ምስራቅ 130 ኪ/ሜ ከደ/ብርሃን 83 ኪ/ሜ እንገኛለን።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
This first-time open tender (No. 01), issued by the Amhara National Regional State, North Shewa Zone, Ensaro District Finance Office for the 2019 budget year, covers 11 lots: office supplies, electronics, cleaning items, sports equipment, water items and fittings, vehicle tires and spare parts, animal medicine and supplies, permanent consumables, lab coats, furniture, and chemical apparatus. The bid document costs 500 birr (non-refundable), and bid bond amounts vary by lot, from 6,000 to 60,000 birr. Proposals must be submitted by the 16th day at 4:00 AM, with the opening held at 4:30 AM the same day. Bidders need a renewed business license, paid current taxes, a TIN, a company seal, and VAT registration when the procurement amount is 200,000 birr or more; the bid validity period is 45 days.
