Tender Detail

Tender Details

  • Company የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ደ/ት/ቤት
  • Address አየር ጤና ታክሲ ተርሚናል ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-8-35-74-96
  • Website
  • Deadline19 Aug 2026, 5:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በእያንዳንዱ ሎት
  • Bid Securityበባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ
  • opening dateበ11ኛው ቀን 4:30 ሰዓት
  • Categories Furniture And Furnishing , Office Supplies And Services , Printing And Publishing

የመማር ማስተማር የሚውሉ ዕቃዎች ግዥ

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ደ/ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2016

በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም 4/ገ/ን/የሥራ ሂደት በጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም መሰረት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የመማር ማስተማር የሚውሉ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የደንብ ልብስ---------------15000.00
ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች----------------- 12000.00
ሎት 3. ህትመት-------------------10000.00
ሎት 4 አላቂ የትምህርት እቃዎች---------------- 15000.00
ሎት 5 አላቂ የፅዳት እቃዎች-----------------5000.00
ሎት 6. የተለያዩ መጻህፍት------------------ 1000.00
ሎት 7 ቋሚ ኤሌክትሮኒከ እቃዎች-----------10000.00
ሎት 8 ፈርኒቸር የቤትና የበሮ ቋሚ ዕቃዎች--------- 10,000.00
ሎት 9. የተለያዩ የጉልበት ስራዎችና የጭነት አገልግሎት——— 1000.00
ሎት 10 ጀነሬተር ፕሪንተር እድሳትና ጥገና--------------- 9000.00
ሎት 11. ጥገና--------------------20000.00

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

  1. በዘርፉ አግባብነት ያለው ሕጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያለው፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ፡፡
  2. በመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገበበትን ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ሠራ ቀናት የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ከግዥ ክፍል መውሰድ ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ ማስገባት አለበት፡፡ ሰነዱ ላይ ፊርማና ክብ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች ከላይ በየሎቱ የተጠቀሱትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው የዕቃ አይነቶች ናሙና ማቅረብ፡፡ በናሙና ለማቅረብ የሚያስቸግሩትን በፎቶ ጨረታው ከመዘጋቱ ቀደም ብለው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የዕቃ አይነቶች ወይም የሚቀርበው የዕቃ መግለጫ /specification/ መሰረት መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ናሙናዎች በጨረታ ለተሸነፉ ተጫራቾች ተመላሽ ይሆናሉ፡፡
  8. ጥቃቅን እና አነስተኛ ዕቃ አቅራቢዎች ከሚመለከተው አካል በት/ቤቱ ስም የተጻፈ ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. አሸናፊው ያሸነፈበትን እቃ ትምህርት ቤቱ የዕቃ መረከቢያ ስቶር ድረስ በራሱ ትራንስፖርት በማቅረብ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  10. ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11:30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  11. አሸናፊው ውል ገብቶ ዕቃዎችን ከማስገባት በፊት ውል የመሰብሰቢያ 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ት/ቤቱ አሸናፊው ድርጅት ላሸነፈባቸው ዕቃዎች 20/100 ብዛት ከውል በፊት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው።
  14. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር - 0118357496/0118387908

አድራሻ፦ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ ደ/ት/ቤት ውስጥ አየር ጤና ታክሲ ተርሚናል ፊት ለፊት

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አየር ጤና አጠቃላይ 2ኛ/ ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
- Procurement: Teaching and learning materials across 11 lots, including uniforms, office furniture, printing, educational supplies, cleaning supplies, books, electronics, household/fixed furniture, labor and transport services, generator/printer renewal and maintenance. - Issuer: Kolfe Keraniyo Sub-city Ayer Health General 2nd School, Addis Ababa. - Dates: Bids close at 11:30 on the 10th day after the announcement; bids are opened at 4:30 on the 11th day. - Costs: Bid document price is 200 ETB per lot (non-refundable). Bid security is a bank-guaranteed CPO, with per-lot amounts ranging from 1,000 to 20,000 ETB. - Requirements: Valid renewed license in the field, current tax payment, registration with the Public Procurement Agency as a goods supplier, VAT registration, and samples for items requiring them. Small and micro enterprises must attach a letter from the relevant body in the school’s name.
Save Tender