Tender Detail

Tender Details

  • Company ኦቢኤም ኮንስትራሽን ድርጅት
  • Address Addis Ababa, Phone: --
  • Website
  • Deadline14 Aug 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Security2%
  • opening date2026-08-15 10:00:00
  • Categories Vehicle

መሥሪያ ቤታችን ለሠራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚውሉ ብዛት 2 (ሁለት) አዲስ ሙሉ በሙሉ በኤሌከትሪክ የሚሠሩ (Fully Electric EV) ተሸከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ኦቢኤም ኮንስትራሽን ድርጅት


የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EV) ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: EV-TENDER PSM001/2018

መሥሪያ ቤታችን ለሠራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚውሉ ብዛት 2 (ሁለት) አዲስ ሙሉ በሙሉ በኤሌከትሪክ የሚሠሩ (Fully Electric EV) ተሸከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ህጋዊ መስፈርቶች

* በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው፤

* የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤

* ወቅታዊ የመንግሥት ግብር የከፈሉበትን ማረጋገጫ (Tax Clearance) ማቅረብ የሚችሉ፤

* በአቅራቢዎች ዝርዝር (Suppliers List) የተመዘገቡ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤

2. የዕቃው ዓይነት እና ብዛት በለጭሩ

* የዕቃው ዓይነት፡ ለሠራተኞች ሰርቪስ የሚሆን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠራ (EV) ሚኒባስ

* ብዛት፡ 2 (ሁለት) 00 ኪሎ ሜትር (Zer Kilometer)

* የመጫን አቅሙ- ከ14-16 ሰዉ- (14-16 person)

3. የጨረታ ሰነድ ስቀራረብ እና መመሪያ

* ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ሜክሲኮ ኮሜርስ ፊት ለፊት በሚገኘው ቢፍቱ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ኦቢኤም ኮንስትራክሽን ድርጅት - ፋይናንስ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

* ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር ሁለት ፐርሰንት (2%) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡

* ተጫራቾች የቴከኒከ እና የፋይናንሻል ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ በማድረግ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይቀናት ወስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

* ጨረታው በ8/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ላይ ተዘግቶ፣ በ9/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅታችን የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ይከፈታል።

* መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ኦቢኤም ኮንስትራሽን ድርጅት

 

✨ messages.ai_summary
- Procurement: 2 new, zero-kilometer fully electric (EV) minibuses for staff service, with 14–16 person capacity. - Issuer: OBM Construction. - Submission deadline: 2026-08-14; bid opening: 2026-08-15. - Bid document price: 1,000 ETB (non-refundable); bid bond: 2%. - Eligibility requirements include a renewed trade license and business registration, TIN and VAT certificate, tax clearance, and registration in the suppliers list.
Save Tender