የጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 3 በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጻም ይፈልጋል፡፡
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጉ/ክ/ከ/ወ/3/ፋይናንስ ጽ/ቤት 001/2019 ዓ.ም
የጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 3 በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጻም ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
ሎት 2. የጽዳት ዕቃ
ሎት 3. የደንብ ልብስ
ሎት 4. የደንብ ልብስ ስፌት
ሎት 5. ህትመት አገልግሎት
ሎት 6. የትራንስፖርት አገልግሎት
ሎት 7. ቋሚ እቃ
ሎት 8. የካፌ አገልግሎትና መስተንግዶ ግዥ
ሎት 9 የኮምፒውተር ፤- ፕሪንተር አና ፎቶኮፒ ጥገና፤ሞንታርቦ ጥገና
ሎት10 የህንፃ አቃዎችና ልዩ ልዩ አቃዎች
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሱ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
1. ሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ዕቃ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
2. የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ 50,000 ብር /ሀምሳ ሺህ ብር/ሎት 2. የጽዳት ዕቃ 50,000 ብር /ሀምሳ ሺህ ብር/፤ ሎት3, የደንብ ልብስ 50,000 ብር (ሀምሳ ሺህ ብር) /ሎት 4. የደንብ ልብስ ስፌት 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ 5. ህትመት 10,000 ብር / አስር ሺህ ብር/፤ሎት6. የትራንስፖርት አገልግሎትı5,000/፤አስራ አምስት ሺህ ብር / ሎት 7 ቋሚ እቃ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሎት8. የካፌ አገልግሎት መስተንግዶ 40,320 (አርባ ሺህ ሶስት _ መቶ ሃያ ብር) ሎት9. የኮምፒውተር ፤ፕሪንተር ፤ፎቶ ኮፒ ጥገና 4,000 (አራት ሺህ ብር ) ሎት 10) የህንፃ እቃዎችና ልዩ ልዩ እቃዎች 5,000(አምስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በጉ/ክ/ከ/ፋይናንስ ጽ/ቤት በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
3. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር የውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው እቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን (10%) በባንከ በተመሰከረ / cpo / ማቅረብ ይጠበቅባችኋል። ይህ ባይሆን ግን በጨረታ ያስያዙት ሲፒኦ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
4. የሚያቀርቡት የዕቃው ዋጋ በሁለት ፖስታዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
5 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 11:30 በወረዳው አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የመከፈቻው ቀን በዓል ወይም እረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
6. የጨረታው ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150 ብር / አንድ መቶ ሃምሳ ብር /በመከፈል ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መውሰድ ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች ለመወዳደር በመረጡት ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በወረዳው ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. የሚቀርበው የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
9. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ማስረጃ ኮፒ የሚታይ መሆን አለበት፡፡
10. አቅራቢ ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት የጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 3 ንብረት ክፍል መድረስ ይኖርበታል፡፡
11. አስተዳደሩ ባወጣው ጨረታ ላይ ከውል በፊት የእቃው ብዛት 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል እንዲሁም ከውል በኋላ ደግሞ 25 የዋጋውን መጨመር መቀነስ ይችላል፡፡ በጨረታ መወዳደሪያ የሚቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ፀንቶ ይቆያል፡፡
12.መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
13.ማብራሪያ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0111-22-26-00 መደወል ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾች ቅድሚያ እንሰጣለን መተጨማሪም መወዳደርየሚችሉት አምራች በሆኑበት የንግድ ዘርፍ ብቻ ነው::
አድራሻ፡- ከመነን ሽሮ ሜዳ በሚወስደው መንገድ ፀሃይጮራ ት/ቤት ፊት ለፌት
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
