Tender Detail

Tender Details

  • Company የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline28 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው የገንዘብ መጠን በየ ሎቱ የተለያየ ነው።
  • opening date2026-07-28 09:30:00
  • Categories Printing And Publishing , Vehicles Rent , Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts

የአ/ቃ/ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን ለሴክተሮች የሚያስፈልጉ የአገልግሎት ግዥዎች /የህትመት ሥራዎች፣ የመኪና ኪራይ፣ የድንኳን እና ዲኮር አገልግሎቶች እና የዋንጫዎች/ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

 

የአ/ቃ/ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን ለሴክተሮች የሚያስፈልጉ የአገልግሎት ግዥዎች /የህትመት ሥራዎች፣ የመኪና ኪራይ፣ የድንኳን እና ዲኮር አገልግሎቶች እና የዋንጫዎች/ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1፡- የህትመት ሥራዎች፤

ሎት 2፡- የመኪና ኪራይ፤

ሎት 3፡- የድንኳን እና ዲኮር አገልግሎቶች፤

ሎት 4፡ የዋንጫዎች ግዥ፤

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1.     በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ

2.     የንግድ ምዝገባ ፍቃድ ያለው

3.     የዘመኑን ግብር የከፈሉና በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

4.     ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

5.     የጨረታ ማስከበሪያ CPO

ሎት፡-1- 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ/

ሎት 2፡- 45,000.00 /አርባ አምስት ሺህ ብር ብቻ/

ሎት 3፡- 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር ብቻ/

ሎት 4፡ 20,000.00/ሃያ ሺህ ብር ብቻ/ ሲፒኦ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ያሰራሉ።ተጫራቾች የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ለሚወዳደሩ ተጫራቾች በሀገር ውስጥ ምርት ላይ ብቻ የተሳተፉ እና ካደራጃቸው አካል ስድስት ወር ያልሞላው የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ በነፃ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የመንግስት ግዢ አስተዳደር ቡድን ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

6.     የአሸናፊው ድርጅት CPO ተመላሽ የሚሆነው የውል ማስከበሪያ የአጠቃላይ ያሸነፈበትን ዋጋ 10% ሲያሲዝ ብቻ ነው።

7.     ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከመስሪያ ቤቱ በገዙት ዋጋ ማቅረቢያ ብቻ በግልጽ እና በሚታይ መልኩ ያለ ስርዝ ድልዝ በመሙላት ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒውን በተለያ የፖስታ በማሸግ ሁለት ፖስታ በአንድ ላይ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) የሥራ ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

8.     በአስራ አንደኛው (11) የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ተጫራጮች ሰነድ በማስገባት 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ልክ 4፡30 ሰዓት ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሁለተኛ ፎቅ ጨረታው ይከፈታል።

9.     መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ፡- አድራሻ ከቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት ባለው የአስተዳደር ህንፃ ላይ ሁለተኛ ፎቅ መጠየቅ ይችላሉ።

 

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender