ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ለምርት ሂደቱ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ጥሬ ዕቃዎች፣ ኬሚካሎች፣ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች፣ መለዋወጫዎች እና ሌሎች የአቅርቦት እቃዎችን በተሻለ ጥራት፣ በተወዳዳሪ ዋጋ እና በተረጋጋ አቅርቦት ለማቅረብ የሚችሉ ብቁ አቅራቢዎችን ለመለየት የቅድመ ብቃት ማረጋገጫ ጨረታ ይጋብዛል፡፡
የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩኘ ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
የቅድመ ብቃት ማረጋገጫ (pre-qualification) ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ለምርት ሂደቱ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ጥሬ ዕቃዎች፣ ኬሚካሎች፣ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች፣ መለዋወጫዎች እና ሌሎች የአቅርቦት እቃዎችን በተሻለ ጥራት፣ በተወዳዳሪ ዋጋ እና በተረጋጋ አቅርቦት ለማቅረብ የሚችሉ ብቁ አቅራቢዎችን ለመለየት የቅድመ ብቃት ማረጋገጫ ጨረታ ይጋብዛል፡፡
በመሆኑም ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ አምራቾች፣ አስመጪዎች፣ አከፋፋዮች እና በተመለከተው ዘርፍ ብቃትና ልምድ ያላቸው ድርጅቶች በዚህ የቅድመ ብቃት ሂደት እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
አመልካቾች ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች
1. የህጋዊ ብቃት ማረጋገጫ
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት
- TIN ሰርተፍኬት
- VAT ምዝገባ ማስረጃ (ተገቢ ከሆነ)
- የግብር ከሊራንስ
2. የቴከኒከ ብቃትና የጥራት ማረጋገጫየሚቀርበው ዕቃ ዝርዝርና ቴከኒክ መግለጫ
- የአምራች መረጃ ወይም የተፈቀደ አቅራቢነት ማስረጃ
- የጥራት ማረጋገጫ
- Certificate of Analysis (CoA) SDS/MSDS (ለሚመለከታቸው እቃዎች)
3. የልምድና የአቅርቦት አቅም
- ተመሳሳይ ዕቃ የማቅረብ ልምድ
- የቀድሞ የአቅርቦት ውል ወይም የደንበኛ ማጣቀሻ
- የማከማቻና የማጓጓዣ አቅም
- የአቅርቦት ጊዜ ማረጋገጫ
4. የአስመጪነትና የአቅራቢነት ማስረጃ
- የአስመጪነት ፈቃድ
- ከውጭ አምራች የተሰጠ የውክልና አቅራቢነት ማስረጃ
- የአምራች ማረጋገጫ ደብዳቤ (ካለ)
5. የፋይናንስ አቅም ማረጋገጫ
- የፋይናንስ አቅም ማስረጃ
- ተመሳሳይ ግዥ ለመፈጸም የሚያስችል አቅም
- ተገቢ የፋይናንስ መረጃ
6. የደህንነትና ህግ ተገዢነት
- የደህንነት መረጃዎች
- የማከማቻና የማጓጓዣ መመሪያዎች
- በህግ የሚጠየቁ ተጨማሪ ፈቃዶች
- ሌሎች በግዥ አካሉ የሚጠየቁ ሰነዶች
- የግምገማ ሂደት የሚቀርቡ ሰነዶች በህጋዊ ብቃት፣ በቴክኒከ አቅም፣ በጥራት፣ በልምድ፣
በፋይናንስ አቅም እና በአቅርቦት ብቃት መሰረት ይገመገማሉ፡፡
ተጫራቾች የቅድመ ብቃት ሰነዶቻቸውን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በቀን ከ07/11/ 2018 እስከ 21/11/2018 ዓ.ም በተከታታይ 15 ቀናት ዉስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የመጨረሻ ማቅረቢያ ቀን፡ 22/11/2018
የማቅረቢያ ቦታ- ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
ማሳሰቢያ፡- ይህ ማስታወቂያ ለቅድመ ብቃት ምዝገባ ብቻ ሲሆን የዉል ሽልማት አይደለም፡፡ ድርጅቱ ያቀረበው ሰነዶችን የማረጋገጥ፤ ተጨማሪ መረጃ የመጠየቅ፤ እንዲሁም ማንኛውንም ወይም ሁሉንም ማመልከቻዎች ያለምንም ግዴታ የመቀበል ወይም ያለመቀበል ሙበት አለው፡፡ መከላኪያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩብ የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ዶኩመንቱ የሚገበዉ በሃርድ ኮፒ ወይም በኢሜይል dhugumafita@gmail.com መሆኑን በአክብሮት እያገለፅን፡፡
በተጨማሪ በስልክ ቁጥር 0999150875 /0969391969 ወይም
+251-11-2-19-00-42 ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
