ጉሌ ውሃን ኮንስትራክሽን ድርጅት _ንብረትነታቸው የድርጅቱ የሆኑተ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ጉሌ ውሃና ኮንስትራክሽን ድርጅት
የተጨራቾች መመሪያ
የጨረታ ቁጥር ጉ.ው.ኮ.ድ 29/09/2018
ጉሌ ውሃን ኮንስትራክሽን ድርጅት _ንብረትነታቸው የድርጅቱ የሆኑተ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል፡፡
1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆኑ ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ማንነቱን የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
2. ተጫራቾች ፒያሳ _ በሚገኘዉ ቢሮኣችን _ በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ቅዳሜም ጨምሮ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሱት መ/ቤቶች በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሸከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው::
5. የጨረታው የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይሆናል፡፡ ይሁንና የተሽከርካሪውን የመነሻ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) ያላስያዘ እንዲሁም በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ዉጭ ይደረጋል፡፡
6. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ ዕዳ ካለበት በባለንብረቱ መሥሪያ ቤት የሚሸፍን ይሆናል፡፡
7. የጨረታ ማስገቢያ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ 8፡10 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፒያሳ በሚገኘዉ ብሮዋችን መከፈቻ ቀኑ ቅዳሜ ላይ ቢዉልም ይከፈታል ፡፡ ነገር ግን የመከፈቻ ቀኑ እሁድ ላይ ከዋለ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይይከፈታል ፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስቀረውም፡፡
8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መከፈል ይኖርባቸዋል፡፡
9. ይሁንና ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል::
10. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል ማሰከበረያ ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አስርበመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ያለበት ሲሆን ከፍያዉ ፍጽሞ ካጠናቀቀ በኋላ ያሰያዘዉ የዉል ማሰከበሪያ ተመላሽ ይሆናል ፡፡
11. ድርጅቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል፡፡
12. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሽከርካሪውን በio (አስር) ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0913456258 በመደወል መረጃ ማገኝት ይችሳሱ
ለሽያጭ የቀረቡ ተሸከርካሪዎች ዝርዝር
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪዉ ዓይነት |
|
1 |
ዳዎ ገልባጭ መኪና Daewoo Truck |
|
2 |
ዳዎ ገልባጭ መኪና / Daewoo Truck |
|
3 |
ባለጎማ ሎደር /wheel loader / |
|
4 |
ባለጎማ ሎደር /wheel loader/ |
ጉሌ ውሃና ኮንስትራክሽን ድርጅት
