አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ /አ.ማ/ የፅህፈት መሣሪያዎች ፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
Africa Insurance Company (S.C.)
አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ /አ.ማ/
የፅህፈት መሣሪያዎች ፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AIC፡-0015/2026
ኩባንያችን የተለያየ መጠን ያላቸውን የፅህፈት መሣሪያዎች ፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች እንዲሁም የህትመት ውጤቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሀ. ሎት -1 የፅህፈት መሣሪያዎች
ለ. ሎት-2 የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እንዲሁም ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የብቃጥ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተገለጸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሲፒኦ (CPO) ሙሉ ለሙሉ ተመላሽ የሚሆነው አሸናፊው ድረጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ለኩባንያው ገቢ ካደረገ በኋላ ኩባንያው የገቡትን እቃዎች በሳምፕላቸው መሰረት መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኩባንያው ዋና መ/ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ሀምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሀምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ድረስ ቦሌ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ በስራ ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ሀምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ/ስልጠና አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ የእቃው ዝርዝር መግለጫ (Specification) የያዘ ሊሆን ይገባል እንዲሁም በሚያቀርቡት ናሙና (Sample) ላይ የድርጅታቸው ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
- አንዱ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታው የሚያሳግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች ከ7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ወይም በውሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች ሲወዳደሩ ባስገቡት (ባቀረቡት) ሳምፕል / ናሙና እንዲሁም የህትመት ውጤት በኩባንያው ናሙና መሰረት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቶች ያሸነፉትን እቃ እንዲሁም የህትመት ውጤቶች የኩባንያው ዋና መ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0116 611877 / 0116 637485 / 0116 637716 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ድርድይ አካባቢ (ሸዋ ሱፐርማርኬት ፊት ለፊት) አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ
