Tender Detail

Tender Details

  • Company Love for Children and Family Development Organization (ላቭ ፎር ችልድረን ኤንድ ፋሚሊ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን)
  • Address ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መካኒሳ ሚካኤል ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያው ጀርባ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0911 12 13 37
  • Websitehttps://love-for-children.org/
  • Deadline15 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-07-15 10:30:00
  • Categories Food And Beverage

ላቭ ፎር ችልድረን ኤንድ ፋሚሊ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን በስሩ ላቀፋቸዉ ህፃናት የሚከተሉትን የምግብ ዓይነቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Love for Children and Family Development Organization (ላቭ ፎር ችልድረን ኤንድ ፋሚሊ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን)


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ላቭ ፎር ችልድረን ኤንድ ፋሚሊ ዴቬሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን ከፕሮጀክት ሆፕ ጋር በአጋርነት የሚሰራ ድርጅት ነው::

ድርጅቱ በስሩ ላቀፋቸዉ ህፃናት የሚከተሉትን የምግብ ዓይነቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ዕቃዎች ማቅረብ የምትችሉ::

1.     ሩዝ በኪሎ የሀገር ውስጥ                                                  700 ኪ.ግ

2.     ኒዶ ወተት 900 ግራም                                                    25 ጣሳ

3.     ዘይት በሊትር ሰን ፍላውር (ባአንድ ሊትር)                              268 ሊትር

4.     ጤፍ በኪሎ (ነጭና ሰርግኛ ለየብቻ)                                    13,400 ኪ/ግራም

በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጸውን መስፈርት የምታሟሉ እንድትወዳደሩ ተጋብዛችሁዋል::

1.     በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3.     በዘርፉ ልምድ ያላችሁ

4.     ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ሰባት ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የጨረታ ሰነዳችሁን ሞልታችሁ እንድታቀርቡ እናሳስባለን::

ማሳሰቢያ

✔ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም::

✔ ተጫራጮች የሚያቀርቧችን የዋጋ ዝርዝር ከሚያቀርቡዋችወ አጠቃላይ ዋጋ ከነቫቱ 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋጋጠ ሲፒዮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::

✔ ጨረታው ሀምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም በ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ይከፈታል::

✔ ሰነዳቸውንና ማስረጃቸውን የድርጅቱን ማሕተም በማስቀመጥና በፖስታ በማሸግ በድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::

✔ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል ::

✔ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::

✔ ጨረታ ላጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ::

✔ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሊሰርዝ ይችላል::

የድርጅቱ አድራሻ

✔ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚያስገቡበት የድርጅቱ ጽ/ቤት በሚገኝበት አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መካኒሳ ሚካኤል ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያው ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይሆናል::

✔ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል:: ለበለጠ መረጃ በሞባይል ቁጥር 0911 12 13 37/ 09 10 64 57 26 መደወል ይችላሉ:: በኢሜል loveforchildrenfdco@gmail.com

Save Tender