Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopiaq, Phone: +251112730852
  • Website
  • Deadline07 Aug 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security1/4ኛውን
  • opening date2026-08-07 14:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Land, House, Building And Warehouse Rent

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ።

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት እነ አቶ ምንዳ አስራት እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ተድባብ አበበ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.184148 በቀን 27/07/2015 ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.188754 በቀን 07/9/2015ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ.188754 በቀን 09/07/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በየካ ከ/ከተማ ወረዳ 1 የቤት ቁጥር አዲስ የሆነ መኖሪያ ቤት 1ኛ ጣልቃ ገብ እና 2ኛ ጣልቃ ገብ ከሰሩት የግል ቤት ውስጥ ያለው የይዞታ ስፋት በካርታቸው 356ካ/ሜ ከፕላን አንጻር ሲረጋገጥ ከአጠቃላይ ይዞታ ላይ ተግባራዊ የሆነ 109 ካ/ሜ የሚቀነስ ቤቱ ለመኖሪያ የሚያገለግል ሲሆን አሁን ባለው ለድርጅት እያገለገለ ያለ 1ኛ ጣልቃ ገብ እና 2ኛ ጣልቃ ገብ ከሠሩት የግል ቤት ውጭ ያለው የውርስ ቤት ብቻ ቤቱና ቦታ በተመለከተ እስከ 2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ግብርየተከፈለ ሲሆን የ2015 ዓ.ም. በጀት አመት በአዲሱ ተመን አስተምኖ የሚከለል ሲሆን ይዞታ በባዩ ወ/ጻዲቅ ስም ተመዝግቦ ይገኛል የሐራጅ መነሻ 15.274.847.40 (አስራ አምስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ አራት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሰባት ከ40/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምከንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.188754 በቀን 30/08/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 3,818,711,85 (ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አስራ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ አስራ አንድ ከ85/100) ሆኖ የትራዛከሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡

የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከı/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

 

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

 

Save Tender