Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline07 Aug 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security1/4 ኛውን
  • opening date2026-08-07 10:30:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Land, House, Building And Warehouse Rent

የቦታ ስፋት 76.5ካ/ሜ የሆነ የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

 

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ትዕግስት እሸቱ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ብርቄ ካሳዬ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/246181 በ2/6/2017 ዓ.ም/እና/በኮ/መ/ቁ/145715 በ25/3/20179/ዓ.ም /በኮ/145715 በ30/06/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 የሚገኝ የካርታ ቁጥር ወ2/ወዝ01/394/10801/00 በሴሪ ቁጥር 001289 የሆነው ይዞታ የክፍሉ መሬት አስተዳደር በ30/06/2018 ዓ.ም ባደረገው ክፍፍል በ"A" የተመለከተው የቦታ ስፋት 76.5ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,282,199.50 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማንያ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ 50/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾF ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከነ/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

 

Save Tender