ነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር ህንፃ መልሶ ግንባታ የአልሙኒየም በርና መስኮቶች ከመስታወት ጋር /Aluminum Doors and Windows With Glass / ስራን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Nebar General Trading PLC
የአልሙኒየም በርና መስኮቶች ከመስታወት ጋር /Aluminum Doors and Windows with Glass / ስራ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ NGTSC/R/004/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ-01 ለሚገኘው ለነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር ህንፃ መልሶ ግንባታ የአልሙኒየም በርና መስኮቶች ከመስታወት ጋር /Aluminum Doors and Windows With Glass / ስራን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በሟሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የዘመኑን የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በስራ ዘርፉ ላይ ሁለትና ከዛ በላይ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ
- ቢያንስ ከሦስት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈፃፀም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ
- በ2017 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,00 ( አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር በነባር አጠቃላይ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር ስም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል እና አንደ ኮፒ ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ በማሸግ በድምሩ አራት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ፊርማ፤ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የታሸገውን 3 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፤ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም የታሸገውን 3 ፖስታ የቴክኒካል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፤ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል)፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለስምንት ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት (Calendar Days) የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር በስራ ሰአት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ድረስ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ-01 መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ በነባር አጠቃላይ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ ላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000184750507 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ የገቢ ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡፡፡ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመቁጠሪያ ቀን (Calendar Days) በመቁጠር በ9ኛው ቀን ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በነባር አጠቃላይ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ማሳሰቢያ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 9ኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከሥራው ጋር ያልተመጣጣነ (unbalanced Bid) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና ነጠላ ዋጋው ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
- በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራጮች የሚሰራውን ስራ በአካል ተገኝተው ማየት /Site Visit / ማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የተጫራቾች መመሪያን በሚያዘው መሠረት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች የሚሰራውን የስራ ናሙና / Sample /ሰርቶ ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ በጹሑፍ ወይም በስልክ ቁጥር +251945986845/+251911246312 ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ – 01 መሀል መርካቶ ከምዕራብ ሆቴል ጀርባ ከሸማ ተራ ህንፃ አለፍ ብሎ ነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ፡፡
