Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline05 Aug 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security1/4ኛውን
  • opening date2026-08-05 14:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Land, House, Building And Warehouse Rent

ቦታው ስፋቱ 47.10ካ/ሜ የሆነ የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

 

የፍ/ባለመበት ታምራት ጥላሁን እና የፍ/ባለዕዳ እነ መ/ር ደባሱ ሰውነት መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 116224 በ24/8/2017 እና በኮ/መ/ቁ/121516 በ4/11/2017ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ቦታው ገላን ሳይት ውስጥ የሚገኝ ስፋቱ 47.10ካ/ሜ የቤት ቁጥር ቢ69/24 የሆነ ባለአንድ መኝታ ኮንደሚኒየም ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,590,604.56 ( አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሺህ ስድስት መቶ አራት ብር ከ56/100) ሆኖ የትራንዛከሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት/ ስም c.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሱ መሆኑን እንገልጻስን፡፡

 

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

 

Save Tender