የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ሰይፉ ቶላ እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ሀይሌ ትዕዛዙ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጕዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/331583 በ10/02/2018 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/05248 በ23/4/2018ዓ/ም እና በቀን በ24/6/2018 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ/19056 በ14/7/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ከ/ከተማ ወረዳ 12 ህንጻ ቁጥር 23 የወለል ቁጥር 8ኛ የቤት ቁጥር BBLI-B23/HN/803 የይዞታ መለያ ቁጥርAA000061207402230803 የቦታ ስፋት 57.77 ካ/ሜ ባለ አንድ መኝታ ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,273,943 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ሶስት) ሆኖ የትራንዛከሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቶች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ አፈ/ጽ ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሱ መሆኑን እንገልጻስን፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
