Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
  • Address ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ማህበራዊ ዋስትና አዲሱ ህንጻ ላይ 11ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-26-31-53
  • Website
  • Deadline02 Jul 2026, 4:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price
  • opening date2026-07-02 16:00:00
  • Categories Construction Works

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤትኮተቤ ሳሊተምህረት አካባቢ ባለው የተቋሙ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ግንባታ ሳይት ላይ ተከማችቶ የሚገኘውን የግንበኛ ድንጋይ መሸጥ ይፈልጋል።


የድንጋይ ሽያጭ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤትኮተቤ ሳሊተምህረት አካባቢ ባለው የተቋሙ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ግንባታ ሳይት ላይ ተከማችቶ የሚገኘውን የግንበኛ ድንጋይ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ማንኛውም ለግንበኛ የሚሆን ድንጋይ መግዛት የሚፈልግ (ገዥ) ከዚህ በታችየተዘረዘሩትን በማየት መግዛት ይችላል።

1.    የአንድ መኪና ቢያጆ የሽያጭ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ ብር 4,800.00 (አራት ሺ ስምንት መቶ ብር) ስለሆነ ገዥው ቢያንስ 05 /አምስት/ ቢያጆ እና ከዛ በላይ ብዛት መግዛት ይችላል።

2.    ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአንድ መኪና ቢያጆ የሽያጭ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ በብር 4,800.00 (አራት ሺ ስምንት መቶ ብር) የ05 /አምስት/ እና ከዛ በላይ ቢያጆ አጠቃላይ ዋጋ በEEU-UEAP A/C No 1000-604742556 ገቢ በማድረግ የኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ዋስትና ንግድ ማዕከል ህንፃ ላይ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ ደረሰኝ ማስቆረጥ ይችላሉ።

3.    ገዥዎች የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት 7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ኮተቤ አካባቢ ባለው የተቋሙ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ግንባታ ሳይት ድንጋዩን የሚጭን መኪና በማቅረብ ድንጋዩን አስጭነው መውሰድ ይችላሉ።

4.    ድንጋዩን በተጫራች መኪና ላይ የመጫን ኃላፍነት የሻጭ ነው።

5.    ድንጋዩን የሚጭን መኪና የማቅረብ ኃላፍነት የገዥ ነው።

6.    ገዥ መግዛት የሚችለው ዝቅተኛው የቢያጆ መጠን 05/አምስት/ ነው።

7.    ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-126 3153 መደወል ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት

Save Tender