በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የሐራጁ ሽያጭ ጨረታው የማካሄድ ይፈልጋል፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ኑኑ ተሾመ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ገነት ተሾመ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይየፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/37518 በ6/04/2007ዓ.ም በኮ/መ/ቁ/115914 በ10/3/2017ዓ.ም በኢቃቂ ቃሊቲ ክ/ተማ ወረዳ 01 የቤ.ቁ 144 የሆነ በእነ ወ/ሮ ዘውዲቱ ተሾመ ባህረ ስም ተደራጅቶ የሚገኝ የይዞታው ነባር ይዞታ ቢሆንም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሌለው (ሰነድ አልባ ይዞታ) አጠቃላይየይዞታው ስፋት 1988ዓ.ም የGIS መረጃ መሰረት 2100 ካ/ሜ ሲሆን በአካል የተገኘ በተወሰደ ልኬት መሰረት 2055 ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 58.339.755 (ሃምሳ ስምንት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ አምስት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክበተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ እሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት /ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክበተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልከ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
