ኤልሳቢ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሰንጠረዡ የተመለከተውን ተሽከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 216/92 እና 1147/2019 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ELSABI Microfinance Institution
ኤልሳቢ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሰንጠረዡ የተመለከተውን ተሽከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 216/92 እና 1147/2019 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የተሸከርካሪው | የሐራጅ መነሻ ዋጋ(ብር) | ሐራጁ የሚከናወንበት
ቀንና ሰዓት |
||||
| ዐይነት | የሞተር ቁጥር | የሻንሲ ቁጥር | የተሠራበት ዘመን | ታርጋ(ሰሌዳ) ቁጥር | ብር 249,874.74 (ሁለት መቶ አርባ ዘጠኝ ሺ ስምንት መቶ ሰባ አራት ብር ከ74/100 ሳንቲም) | መስከረም 27/2018ዓ.ም
ከጠዋቱ 4፡00 እሰከ ጠዋቱ 5፡30 ስዓት |
|||
| ሀ/ሚካኤል አባተ ያዘው | ተበዳሪው | አዲሱ ገበያ | አውቶሞቢል | LF479Q3*080500001 | LLV2A2A1080034590 | 2010 | አ.አ3-B64063 | ||
የጨረታ ደንቦች
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከተቋሙ በማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በካሽ በመክፈል ከተቋሙ ዋና ቢሮ ቀርቦ መውሰድ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ የብር መጠን ¼(አንድ አራተኛ) በተረጋገጠ የባንክ የክፍያ ማዘዣ/ሲ.ፒ.ኦ/ በኤልሳቢ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ሐራጁ የሚከናወነው አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጃክሮስ አካባቢ ወደጎሮ መታጠፊያ 100 ሜትር ገባ ብሎ ብርሃን ባንክ ያለበት ሕንፃ ጎን የሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ነዉ:፡
- የንግድ ማህበራትን ወክሎ ለመጫረት የማህበራቱን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበራቱ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል::
- ተበዳሪው (መያዣ ሰጭው) በሃራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገርግን ባይገኙም ሃራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- ንብረቱን ለመጎበኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ፕሮግራም በማስያዝ በስራ ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በመገኘት መጎብኘት ይችላሉ::
- የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለተቋሙ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- ለጨረታ የቀረበውን ተሸከርካሪ አሸንፎ የገዛ ተጫራች ከገዛው ተሽከርካሪ ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያዎች፣ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ከስም ዝውውር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላል፡፡
- ተሽከርካሪውን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን (ተሸከርካሪውን) ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ተቋሙ ኃላፊነት አይወስድም:: ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል::
- ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር01166675793/0116732829 ይደውሉ፡፡
