Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Women Association (የአማራ ሴቶች ማህበር)
  • Address ባህር ዳር በሚገኘው አማራ ሴቶች ማህበር ዋናው መ/ቤታችን ቀበሌ 13 ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0942835840
  • Websitehttps://amharawomenasso.org.et/
  • Deadline30 Jun 2026, 4:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-07-03 14:30:00
  • Categories Vehicle

የአማራ ሴቶች ማህበር በሥሩ ለሚገኝ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተሽከርካሪ ይፈልጋል::

Amhara Women Association (የአማራ ሴቶች ማህበር)


አማራ ሴቶች ማህበር

Amhara women Association

ቁጥር/Ref:-አሴማ/08/ሰ/ለ-5

 

              የተሽከርካሪ የጨረታ ማስታወቂያ               .

 

የአማራ ሴቶች ማህበር በሲቪል ማህበረሰብ አዋጅ ቁጥር194/2004 አንቀጽ 63 (1) መሰረት የአማራ ሴቶች ማህበር የኢትዮጲያ ማህበር ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን የመዝገብ ቁጥር 016 ነው። የአማራ ሴቶች ማህበር በሁሉም የአማራ ክልል ዞን፤ ወረዳ እና ቀበሌ የተለያዩ የልማት ስራዎች የሚያከናውን ዘርፈ ብዙ የልማት ድርጅት ነው። ድርጅታችን በአሁኑ ሰዓት ከ6 ፕሮጀክቶች በላይ በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳ እና ቀበሌዎች በመተግበር ላይ ይገኛል። በዚሁም መሠረት ድርጅቱ በሥሩ ለሚገኝ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተሽከርካሪ ይፈልጋል:: በመሆኑም የተለየዩ ተሸከረካሪዎች ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾችን ጨረታው ላይ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል::

1.     ተጫራቾች በዘርፋ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ አና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር/ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ /ክሊራንስ/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች እነዚህን እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃወች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በማጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይኖርባቸዋል።

2.     ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ሰኔ 26/2018 ከሰአት 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጨረታዉ ባህር ዳር ባለው ዋና መ/ቤት ይከፈታል።

3.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ጨረታ ሰነዱን ሲወስዱ በሚሰጣቸው የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ሞልተው ማለትም የዋጋ ሰነዳቸውን (በሰም በታሸገ ፖስታ ኤንቨሎፕ) ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4.     ተወዳዳሪዎች የፋይናንስ እና የቴክኒክ መስፈርቶችን በተለያዩ ፋይሎች በተዘጋጀ ሁኔታ ማቅረብ አለባቸው።

5.     ተጫራቾች የሚያቀርቡበት ጊዜ /delivery time/ ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ5 /አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቻ ይሆናል።

6.     ተጫራቾች ሰነዱን ባህር ዳር በሚገኘው አማራ ሴቶች ማህበር ዋናው መ/ቤታችን ቀበሌ 13 ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት በጋዜጣዉ ላይ በተጠቀሱት ቀናት መሰረት ከጠዋት 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰአት በኋላ 7፡00 ሰዓት አሰከ 10፡00 ሰአት የሚያገኙ ይሆናል። የጨረታ ሰነዱን ባህር ዳር በሚገኘው ዋና መ/ቤት ከፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።

7.     ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0942835840/0918780155

Save Tender