የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ሰብአዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን ከዚህ በታች የተገለጸውን የተሽከርካሪ ግዥ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን (Ethiopian Kale Heywet Church Development Commission)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ሰብአዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን ከዚህ በታች የተገለጸውን የተሽከርካሪ ግዥ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የተሽከርካሪ ግዥ
|
የተሽከርካሪው አይነት Type of vehicle |
ብዛት Quantity |
ሞዴል/መጣለጫ Model |
|
ባለ ሁለት ጋቢና ተሸከርካሪ Double-Cabin vehicle (pickup) Four-wheel Drive |
1 |
P2024/2025 G.C |
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉና ቀጥሎ የተገለጸውን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች ለመወዳደር ምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት
3. የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፊኬት
4. የታክስ ክሊራንስ ሰርተፊኬት
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድና መመሪያ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ እየከፈሉ ከልማት ኮሚሽኑ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 102 መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለሚወዳደርሩባቸው የተሸከርካሪ ግዥ ለእያንዳንዱ ከቫት በፊት እና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ በማስቀመጥ የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ለመስሪያ ቤቱ የኦፕሮሽን ክፍል ቢሮ ቁጥር 102 ማስገባት፡፡
7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በአስራ አንደኛዉ ቀን ከጧት 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከጧት 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. ጨረታው ያበቃበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጧት 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
9. መስረያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተከርስቲያን ሰብአዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን
ሜክስኮ/ ከአፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት
ስልክ:- 0115539983/0984798165/
የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ሰብአዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን
