Tender Detail

Tender Details

  • Company Nile Insurance Company S.C (ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)
  • Address ዋናው መ/ቤት ለገሐር (ብሔራዊ ቲአትር አካባቢ) ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ /22ኛ ፎቅ/ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114-42 60 00
  • Websitehttps://nileinsurancesc.com/
  • Deadline27 Jun 2026, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-06-26 00:00:00
  • Categories Vehicle

ጉዳት/አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ተገቢውን ካሣ ከፍሎ በውክልና የተረከባቸውን ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የተሸከርካሪ አካሎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

Nile Insurance Company S.C (ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ)


                                                   የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 158/2018)

                                                         ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

NILE INSURANCE COMPANY S.C

ጉዳት/አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ተገቢውን ካሣ ከፍሎ በውክልና የተረከባቸውን ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ የተሸከርካሪ አካሎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: የተሽከርካሪ የስም ማዛወሪያ፣ የጉምሩክ ቀረጥ፤ ግብርና ሌሎች ዕዳዎችና ወጪዎች ቢኖሩ በአሸናፊው የሚሸፈኑ ይሆናል::

 

የተሽከርካሪ የስም ዝውውር በገዢ ምክንያት ከስድስት ወር በላይ ቢቆይ በዚህ ምክንያት ለሚመጣ ኩባንያችን ኃላፊነት አይወስድም:: አሸናፊ ተጫራች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማቅረብ ይኖርበታል::

 

  1. ንብረቶቹ የሚገኙበት የኩባንያው ሪከቨሪ አድራሻ፡-

ገላን ሪከቨሪ ፡ ገላን ኖክ ፊት ለፊት ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በሥራ ሰዓት ሄዶ በማየት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍሎ መውሰድ ይችላል:: የጨረታ መነሻ ዋጋ 15% ቫት ያላካተተ መሆኑን እየገለጽን፤ ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን የእያንዳንዱን ምድብ እቃ ዋጋ (ቫት ሳይጨምር) በጨረታ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት ለእያንዳንዱ ምድብ እቃ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 20% (ሃያ ከመቶ) በኩባንያው ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የኢንሹራንስ ቦንድ ጋር በኤንቨሎፕ በማሸግ እስከ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀነ 11 ሰዓት ድረስ ብቻ የኩባንያው ዋና መ/ቤት በሚገኝበት ብሔራዊ ቲያትር ከንብ ባንክ ቀጥሎ ባለው ህንፃ ምድር ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል:: ማሳሰቢያ፦ አሸናፊ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ 15% ቫት የሚጨመር መሆኑን እንገልፃለን:: ጨረታው ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ብሔራዊ ቲያትር ከንብ ባንክ ቀጥሎ ባለው ህንፃ በኩባንያው ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ 21ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4 እና 5 ከጠዋቱ በ3፡00 ስዓት ይከፈታል:: ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ሙሉ በሙሉ የሚመለስ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ከሚገዙበት ዋጋ ጋር ይታሰባል:: ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በአሥር ቀናት ውስጥ ክፍያውን አጠናቀው ንብረቱን ባያነሱ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል:: ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111407171/09-11-82-05-76/ በመደወል መጠየቅ ይችላል::

                                                                   ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

 

Save Tender