Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: +251910474668
  • Website
  • Deadline02 Jul 2026, 10:30 AM
  • magazineADDIS zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security2%
  • opening date2026-07-02 10:30:00
  • Categories Vehicle tire , Electrical Materials , Vehicle Spare Parts

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎትየስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዘን እንዲሁም በሜከሲኮ አካባቢ በሚገኝ መጋዘን ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ጎማዎች፣ ያገለገሉ የመኪና መለዋወጫዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት


በድጋሚ የወጣ ያገለገሉ ዕቃዎች

ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዘን እንዲሁም በሜከሲኮ አካባቢ በሚገኝ መጋዘን ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ጎማዎች፣ ያገለገሉ የመኪና መለዋወጫዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም

1)    ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ቤት ቅጥር ግቢ የፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ከፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ እየር ላይ ከዋለበት ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 25/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡

2)    በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች

1.     አገልግሎት /Refugees and Returnees Service / በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንh ዋስትና /Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3)    ማንኛውም ተጫራች ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 25/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጉለሌ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም፡፡

4)    ጨረታው ጉለሌ እንቁላል ፋብሪካ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሰኔ 25/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።

5)    የጨረታ አሸናፊ ተጫራቶች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋሰትና በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

6)    ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው::

7)    በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጨራች ለጨረታው ማስከበርያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8)    አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9)   ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251910474668 ወይም 251911569913 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

Save Tender