የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አዉትቶሀል።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ ባለመብት አቶ ኃይለማርያም ዓለም እና የፍ/ባለዕዳ አቶ እንዳለ ብዙነህ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፈደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/142983 3/11/2016ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/144389 10/11/2016ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሸገር ለገጣፎ ለገዳዲ ከ/ከተማ በካርታ ቁጥር L/XL/D/211882 የሆነውን በፍርድ ባለዕዳ ባለቤት በወ/ሮ ትዕግስት እሸቱ ፈለቀ ስም የተመዘገበ ቤት የሌለው ባዶ ይዞታ የቦታ ስፋት 250 ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1.135.375 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ አምስት) ሆኖ የትራዛከሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 15 ቀን 2018ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡' በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር+251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
