የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የፍ/ባለመብት/አቶ ሙባረክ ረዲ እና በፍ/ባለዕዳ እነ እቶ ተስፋዬ አለኸኝ መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.122176 በቀን 24/2/2018ዓ.ም የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አዉጥቶሀል።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት/አቶ ሙባረክ ረዲ እና በፍ/ባለዕዳ እነ እቶ ተስፋዬ አለኸኝ መካከል ስላለው የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.122176 በቀን 24/2/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ውስጥ የሚገኘው ቤት የመለያ ቁጥርAA000070704783 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታ ስፋት 345 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ 12,001,188 (አስራ ሁለት ሚሊዮን አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ስምንት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.122176 በቀን 02/10/2018ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ 3,000,297( ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና ሰባት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቶች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቶች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡ 30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ c.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
