Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline17 Jul 2026, 3:00 PM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security50,000.00
  • opening date2026-07-17 15:30:00
  • Categories Food And Beverage

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሀዋሳ ኤርፖርት ፓይለት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት (PTSC) ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የስጋ ምርት አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ስምምነት ለሦስት (3) ዓመት ለመሥራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: SSNT-T622

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሀዋሳ ኤርፖርት ፓይለት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት (PTSC) ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የስጋ ምርት አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ስምምነት ለሦስት (3) ዓመት ለመሥራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

በአገልግሎቱ ዘርፍ ለመሠማራት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው ፤ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፊቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ምዝገባ ወረቀት ያለው፣የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣ ሁለት (2) ዓመትና እና ከዚያ በላይ የሠራ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይየሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T622 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሀምሳ ሺህ ብር (50,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቛም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንከ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴከኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እና የጨረታ ማስከበሪያ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ክፍል ሀምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡


ለተጨማሪ ማብራሪያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ 011-517-4552

አሊ አስፋው
ኢ-ሜይል: Alias@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

Save Tender