Tender Detail

Tender Details

  • Company የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም
  • Address ይ/ዓለም ከተማ : ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-225-24-03
  • Website
  • Deadline01 Jul 2026, 4:30 PM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security100,000.00
  • opening date2026-07-01 16:40:00
  • Categories Food And Beverage

በሲ/ብ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሸን የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ከሐምሌ 1/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ድረስ ለ12 (አሥራ ሁለት) ተከታታይ ወራት የሚቆይ ለሕግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል እህል ምግብ ማጣፈጫዎች እና የምግብ ማብስያ ማገዶ እንጨት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም


ለሕግ ታራሚዎች ቀለብ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ ቁጥር 03/2018


በሲ/ብ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሸን የይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ከሐምሌ 1/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ድረስ ለ12 (አሥራ ሁለት) ተከታታይ ወራት የሚቆይ ለሕግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል እህል ምግብ ማጣፈጫዎች እና የምግብ ማብስያ ማገዶ እንጨት ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተመለከቱትን፡-

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

መለኪያ

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

መለኪያ

1

ነጭ ጤፍ

በኩ/ል

10

ዝንጅበል

በኩ/ል

2

ቦቆሎ 1ኛ ደረጃ

በኩ/ል

11

ሻይ ቅጠል ባለ 80 ግራም

በካርቶን

3

ባቄላ 1ኛ ደረጃ

በኩ/ል

12

የእንጀራ ምጣድ

በቁጥር

4

ፊኖ ዱቄት 1ኛ ደረጃ

በኩ/ል

13

ሠፈድ

በቁጥር

5

ዛላ በርበሬ (ያልተፈጨ)

በኩ/ል

14

ካመራ 500 ግራም

በፓኬት

6

የምግብ ጨው

በኩ/ል

15

እርድ

በኩ/ል

7

ጎመን ዘር

በኩ/ል

16

በቀርከሃ የተሰራ አክንባሎ

በቁጥር

8

ቀይ ሹንኩርት

በኩ/ል

17

ሚስር

በኩ/ል

9

ነጭ ሹንኩርት

በኩ/ል

18

የማገዶ እንጨት

በሜ/ኩብ

 ሕጋዊ ተወዳዳሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ _ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ጨረታው የሚካሄድበት የሥራ ቋንቋ አማርኛ ሲሆን በሚወዳደሩበት የንግድ ሥራ ዘርፍ ሕጋዊ የጅምላ ንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው ፣ የግብር ከፋይነት ማስረጃ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የ2018 ዓ.ም ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፤ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ ፤ በጨረታ መወዳደር የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት ዝርዝር ለመመዝገባቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 ( አንድ መቶ ሺህ ብር) የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉና በጨረታ የተጠቀሱ _ መሥፈርቾችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400/አራት መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታውን ሠነድ ከይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ገዝተው ከሞሉ በኃላ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ አሥራ አምስተኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ድረስ የታሸገውን ኤንቬሎፕ ወደ ጨረታ ሳጥን አስገብተው በዚሁ ቀን በዕለቱ 10፡35 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኃላ በዕለቱ 10፡40 ሰዓት ላይተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይርጋዓለም ማረሚያ ተቋም ይከፈታል። ጨረታውን ሰነድ ለውድድር አቅርበው ከግል ፍላጎታቸው /ሁኔታ/ የተነሳ በዕለቱ የማይገኙ ሲሆን ጨረታው ተከፍቶ ውጤቱ ይገለጽላቸዋል እንጂ የጨረታውን ሂደት የሚያስተጓጉል ነገር አይኖርም፡፡ አንድ ተጫራች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡ በጨረታው ሠነዱ የተመለከቱትን ዓይነቶች ከላይ በሰንጠረዥ ውስጥ የተገለጸው መሰረት ይሆናል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸ ጊዜ ጅምሮ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ አቅርበው ውል መፈጸም አለባቸው፡፡ አሸናፊዎችን አሸናፊነታቸውን እንደተገለጸ ውል የማይፈጽሙ ሲሆን ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ አይመለስም (ይወረሳል)፡፡የጨረታው ዝርዝር በጨረታው የአፈጻጸም መመሪያ ላይ የተገለጸ ስለሆነ በይበልጥ ተቀባይነት ያለው የጨረታ ሰነድ በመሆኑ አንድ በአንድ ማንበብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታ አውጪው መ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፡- 046-225-24-03 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

የይርጋለም ማረሚያ ተቋም

Save Tender