Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ
  • Address ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 924955389
  • Website
  • Deadline25 Jun 2026, 10:30 AM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security500,000.00
  • opening date2026-06-25 23:00:00
  • Categories Electronics Materials

.በኢ.ፌ.ዲ. ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት በሀገርውስጥ የሚፈፀሙ ለታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካ ግብዓት የሆነውን የትራንስፎርመር ኢናሜልድ ዋየር (diameter 1.5 mm and 1.8 mm) ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ


ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ


1.በኢ.ፌ.ዲ. ሪ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት በሀገርውስጥ የሚፈፀሙ ለታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካ ግብዓት የሆነውን የትራንስፎርመር ኢናሜልድ ዋየር (diameter 1.5 mm and 1.8 mm) ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

2.
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዟችኋል

3.
በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤

4.
የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

5.
ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡

6.
የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ማስረጃ ማቅረብ አለበት

7.
ተጫራቾች በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስም በብሔራዊ ባንከ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሎት -1 -የትራንስፎርመር ኢናሜልድ ዋየር (diameter 1.5 mm and 1.8 mm) 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለየብቻው ከሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

8.
ተጫራቶች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትከከል መሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለበት፡፡

9.
ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት፡፡

10.
ተጫራቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢከፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ አንደኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ሰነዱን በሶፍት ኮፒ መግዛት ይችላሉ፡፡

11.
ተጫራቶች በገዙትና በሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፁትን ሆኔታዎች በአግባቡ በመጠቀም የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

12.
ተጫራቾች የጨረታ የሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ኤንቨሎፕ አሽገው 2ኛ ፎቅ ላይ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

13.
ተጫራች ለጨረታ ሰነዱ ቴከኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዱን ለየብቻ ለይተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

14.
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይዘጋል፡፡ በዚሁም ዕለት ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

15.
የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

16.
ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60 (ስልሳ) ተከታታይ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህንኑ አውቀው ስለመቀበላቸው በቴከኒካል ኦርጅናል ሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

17.
ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም፡፡ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፦ ለቡ መብራት ኃይል ከጀነራል መርከንታይል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን ስልከ: +251 924955389 +251 910162733 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ



ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ

Save Tender