የደብብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከሐምሌ 01/2018 እስከ ህዳር 30/2019 ድረስ ለ5 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት እንዲሁም ጥሬ እህል ፡ የማጣፈጫ ሸቀጣ ሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
የደብብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ ከሐምሌ 01/2018 እስከ ህዳር 30/2019 ድረስ ለ5 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት እንዲሁም ጥሬ እህል ፡ የማጣፈጫ ሸቀጣ ሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማህበራትም ሆነ ግለሰብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያ ማሟላት አለባቸው፡፡
1. በንግድ ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡ የግብር ከፋይነት (TIN NO ) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ወይም የቫት ከፋይነት እንዲሁም የምዝገባ ምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዞኑ ማረሚያ ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየርላይ ውሎ በ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የህግ ታራሚዎች ኮሚቴ የማረሚያ ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ እና ከዞኑ አቃቢ ህግ ቢሮ እንዲሁም ከዞኑ ገ/ኢ/ትብብር በሚወከሉ በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መስሪያቤቱ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
5. በበሰለ ምግብ አቅርቦት በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ።
6. ጥሬ እህል ለማቅረብ ለሚወዳደሩ የእህሉን ናሙና እና የሚወዳደሩበትን አይነት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለጨረታው ያቀረቡትን ሀሳብ መቀየር ወይንም ማሻሻል እንዲሁም ከጨረታው እራስን ማግለል አይችሉም፡፡
8. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት አንስቶ በ3 ቀን ውስጥ ማረሚያ ቤት በመቅረብ ውልመፈረም ይኖርበታል ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የመጠቀም መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. የበሰለ ምግብ ለማቅረብ ያሸነፈው ማህበር ወይም ግለሰብ ጥራቱን የጠበቀና ለአንድ ሰው የሚሆን ማረሚያ ቤቱ ባወጣው ሜኑ መሰረት አቅርቦት መመገብ አለበት፡፡
10.ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞኑ ማረሚያ ቤት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳይን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
11.ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያውና የውል ማስከበሪያ በጥቃቅንና አነስተኛ ደንብ 192/2009 ተሻሽሎ በወጣው አንቀፅ 27 መሰረት ከአደራጀው ከፍል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው
12.ግለሰብም ሆነ ድርጅት ከሆኑ የጨረታ ማስከበሪያውን 2% በጥሬ ገንዘብ (በባንክየተመሰከረለት CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል ። ለውል ማስከበሪያ 10 % በጥሬ ገንዘብ (በባንከ የተመሰከረለት CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
13.ምግቡ የሚዘጋጀው በመስሪያቤቱ ማብሰያ ውስጥ ሆኖ ለማብሰያ የሚያገለግሉ ዕቃዎች የማረሚያ ቤቱ እንዳለ ሆኖ የጎደለውን ጨረታውን ያሸነፈው ማህበር ወይም ግለሰብ コ ማሟላት ግዴታ አለበት፡፡
14.ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከታች በተገለፀው አድራሻችን ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
15.ተጫራቾች በጫረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ ካላቸው ለማ/ቤቱ ለበላይ አካሎች ጨታው ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ እስከ 5 ቀን ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ማቅረብ ይችላል፡፡
16.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ የደ/ም/ሸ/ዞን/ገ/ኢ/ልማት/ትብብር ፅ/ቤት ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር
011-341-1190
011341-00-23
የደብብ ምዕ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤት መምሪያ
