ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት:-የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማዎች ግዥ ግልፅ ጨረታ መመሪያ ድርጅታችን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፓርት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዕ.ደ.ት.ድ. ግዥ 009/18
የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማዎች ግዥ ግልፅ ጨረታ መመሪያ ድርጅታችን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት ተጫራቾች:-
1. ተጫራች የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርበታል፤
2. ተጫራች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ እና የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪ ጎማዎች አቅርቦት ስለመፈጸሙ የሚያረጋግጡ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስ ሂ/ደ/የስ/ሂ/ዳይሬክቶሬት መግዛት ይቻላል፤
4. ተጫራቾች ከዚህ ደብዳቤ ጋር በአባሪነት በቀረበው የሥራ ዝርዝር ላይ የሚወዳደርበትን ዋጋ ነጠላ ዋጋ (Unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total Price) በግልፅ አሃዞችን በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት ይህ የጨረታ ጥሪ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት እየር ላይ ቆይቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስተጫራቾች ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴከኒካል ኦርጅናል ፣ቴከኒካል ፕሮፖዛል ኮፒ ፣ፋይናሺያል ኦርጅናል ፣ፋይናንሺያል ኮፒ በማለት ለይተው በተለያየ ፖስታ በማድረግ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በግዢ ዲፓርትመንት ዳይከቶሬት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤በዚሁም ዕለት ከቀኑ 8፡30 ጨረታ ይከፈታል፡፡
5. ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ናሙና ከ70% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
6. ተጫራቾች የፋይናንሺያል ሰነድ 30% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
7. የቴከኒክ ግምገማ ውጤት 70/100 ወይም 51/70 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተጫራቾች ለፋይናሺያል ውድድር ግምገማ ያልፋሉ፡፡ በፋይናንሺያል ግምገማ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተጫራቾች አሸናፊ ይሆናሉ ፡፡
8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ የመወዳደሪያ ዋጋ ተደርጎ ይወሰዳል፤
9. በተጫራች የሚቀርብ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፤
10. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጡት ዋጋ መለወጥ ሆነ ማሻሻል አይችሉም፤
11. ማንኛውም ተጫራች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፤
12. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለምን ያህል ጊዜ እንዲሚቆይ በጨረታው ሰነድ ላይ መግለፅ አለባቸው
13. ተጫራቾች በሠንጠረዥ ላይ የተመለከተውን የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማዎች
በመጥቀስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ በባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የሚጫረቱበትን የእያንዳንዱ ሎት፤ ለተለያየ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ተጫራጭ ውጤቱ በፁሁፍ እንደተገለፀለት በ7 (ሰባት) የሥራ ቀናት ውስጥ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና (ፐርፎርማንስ ቦንድ) ከጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ በማስያዝ በግንባር ቀርበው የተዘጋጀውን ውል በመፈረም በ15 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ንብረት ሙሉ አቅርቦት መፈጸም ይኖርበታል፤
15.ተጫራች የተለያየ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪ ጎማዎች የዋጋ ማቅረቢያ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርበታል፤
16. አሸናፊ ተጫራች የተበላሸ የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪዎ ጎማዎች የማስተካከል/የመቀየር ግዴታ ይኖርባታል፤
17. አሸናፊ ተጫራች የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪ ጎማዎች በሙሉ ዋና መ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፤
18. አሸናፊ ተጫራች በገባው ውል መሰረት በ15 ቀናት ውስጥ ንብረቶችን ባያስረከረብ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፤
19. ያላሸነፉ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ውጤቱ እንደተገለፀ ወዲያውኑ 100% ገንዘብ ተመላሽ ይደረግለታል፤
20. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፤
21. ድርጅቱ ይህንን ጨረታ ለአሸናፊ በሚሰጥበት ጊዜ የተለያዩ መጠን ያላቸው የከባድ ተሽከርካሪ ጎማዎች የመግዣ የነጠላ ዋጋ ሳይቀየር ብዛት በ20% ለመጨመር/ለመቀነስ መብት አለው፤
22. ተጫራቾች የጨረታው ስነ-ስርዓት ከመጀመሩ በፊት ስለጨረታው ሂደትና ከጨረታው ጋርየተገናኙ ጉዳዮችን በማንሳት ጥያቄ ማቅረብ መብታቸው ሲሆን፣ የጨረታ ስርዓት ከተጀመረ በኋላ የጨረታውን ሂደት ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ሆነው ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳል፤
23. ድርጅቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡-
በስልክ ቁጥር 011 4 39 00 75/35 92/15 69/011 439 10 27
ፋክስ 011 439 63 36/0114 74 71 41ፖ.ሳ.ቁ. 2562 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ቃሊቲ ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት 70 ሜትር ገባ ብሎ
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት
