አይሬ ኮንሰልቲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (ARE CONSULTING PLC) ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች/አገልግሎቶች አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
አይሬ ኮንሰልቲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር AC/NCB/GOODS/06/2026
አይሬ ኮንሰልቲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (ARE CONSULTING PLC) ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች/አገልግሎቶች አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ድርጅቱ በንግድ ምዝገባ ቁጥር AA-CATB/2/0268907/2018 እና በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) 0106895400 የተመዘገበ ሲሆን፣ በሚከተሉት የንግድ ዘርፎች የሀገር ውስጥ ንግድ ወኪል፣ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረት ኮሚሽን/ብሮከር፣ ልዩ ዝግጅት ማስተባበር፣ እንዲሁም ኢኮኖሚ፣ ቢዝነስና ኢንቨስትመንት ልማት የማማከር አገልግሎት ለመሠማራት ፈቃድ አለው፡፡ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
ሎቶች፡-
1. ሎት ቁጥር 1 – ህትመት አገልግሎት (Printing Service)
2. ሎት ቁጥር 2 – የቢሮ ዕቃዎች (Stationary Materials)
3. ሎት ቁጥር 3 – የንጽህና እና መጸዳጃ ቁሳቁሶች (Sanitary & Hygiene)
4. ሎት ቁጥር 4 – አይቲ መሣሪያዎች (IT Equipment)
5. ሎት ቁጥር 5 – የቤት/ቢሮ ዕቃዎች (Furniture)
6. ሎት ቁጥር 6 – ፊልም ቀረጻ እና ፎቶግራፍ (Filming & Photography)
የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች
1. ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ/ኢንቨስትመንት ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (TIN) ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት 1,500 ብር (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) በማይመለስ መልኩ ይህ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር * ጊዜ ውስጥ ወደሚከተሉት የባንክ አካውንቶች በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
ብርሃን ባንከ (Birhan Bank) አካውንት ቁጥር: 2500110176132
የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ፡
ቴሌብር (Telebirr) ቁጥር: +251991501655 ከፍያ ከፈጸሙ በኋላ የባንክ አድቫይስ (Bank Advice) ወይም የቴሌብር ማስረጃ በዋትሳፕ ወይም በቴሌግራም ወደ ቁጥር +251991501655 መላከ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን ካደረጉ በኋላ ሰነዱ በኤሌክትሮኒከ መንገድ ይላክላቸዋል ወይም በአካል ቢሮ መጥተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. እያንዳንዱ ተጫራች ለሚሳተፍበት ሎት ከጠቅላላ ጨረታ ዋጋ 2% ወይም ቢያንስ 10,000 ብር (የትኛው ቢበዛ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንከ ዋስትና በአይሬ ኮንሰልቲንግ ኃ/የግ/ማህበር ስም ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት [ይህ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን ጀምሮ ከአንድ ወር _ በኋላ በሚቀጥለው ቀን] ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በአይሬ ኮንሰልቲንግ ኃ/የግ/ማህበር ጎላጎል ታወር 9ኛ ፎቅ ቁጥር901 አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
5. አሸናፊው ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያው ከግዢ ዋጋ ጋር ሲታሰብ ይቀመጣል፤ ለተሸናፊዎች የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
6. አሸናፊው ዕቃዎቹን እንዲያነሳ ከተነገረው በኋላ በአሥር (10) የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን ገቢ በማድረግ መውሰድ አለበት፤ ካልሆነ ጨረታው ይሰረዛል፤ የጨረታ ማስከበሪያወም ለኩባንያው ገቢ ይሆናል፡፡
7. ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ለተጨማሪ ማብራሪያ የአይሬ ኮንሰልቲንግ ኃ/የግ/ማህበር ግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት፡
*ስልክ ቁጥር: +251991501655 (ዋትሳፕ/ቴሌግራም)
*ኢሜይል: aireconsultingl@gmail.com
*ወይም በአካል ጎላጎል ታወር 9ኛ ፎቅ ቁጥር 901 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አይሬ ኮንሰልቲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
