Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline07 Jul 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን
  • opening date2026-07-07 11:00:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

 

የፍ/ባለመብት እነ ጌታሁን በጅጋ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ተስፋዬ በጅጋ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/252063 በ4/10/2017ዓ.ም እና በመ/ቁጥር/271660 በ02/04/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 786 በአቶ በጅጋ ቶሎሳ እና ወ/ሮ እልፍነሽ ገብሩ ስም የተመዘገበ የካርታ ቁጥር አ/38207/01 የቦታ ስፋት 289ካ/ሜ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 12,473,514 (አስራ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ሰባ ሶስት ሺህ አምስት መቶ አስራ አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

 

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፈዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደረጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

Save Tender