Tender Detail

Tender Details

  • Company የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
  • Address , Phone: 0114403434
  • Website
  • Deadline16 Jun 2026, 4:00 AM
  • magazineadiss zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን አልተጠቀሰም ።
  • opening date2026-06-16 04:30:00
  • Categories Office Equipment

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች በጅምላ መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ


የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች በጅምላ በመነሻ ዋጋ በማስቀመፕ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሠነድ

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች በጅምላ መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በሽያጭ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቶች መመሪያ የማከበርና የመፈፀም ግዴታ አለባቸው::

ክፍል አንድ

የተጫራቾች መመሪያ

1.     ይህ ጨረታ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሊሳተፍበት ይችላል፡፡

2.     ተጫራቾች መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3.     በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የሥራ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡

4.     ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የሥራ ቀናት ጠዋት ከ3፡00 እስከ 6፡00 ሰአት ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ቃሊቲ ቶታል አካባቢ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ቋሚ ግምጃ ቤት እና ወርቁ ሰፈር (ውሃ ልማት ገባ ብሎ መስጊድ አጠገብ) በእካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡

5.     አንድ ተጫራች የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች በጅምላ በተቀመጠው መነሻ ጥቅል ዋጋ መሰረት በማድረግ የሚገዛበትን የጥቅል ዋጋ በማስገባት መጫረት ይኖርበታል፡፡

6.     ጨረታው ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው (በዕለቱ) በ4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ግቢ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቶች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

7.     ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8.     ተጫራቶች ከጨረታ ሰነዱ ጋር የመታወቂያ እና የጨረታ ሰነድ የዙበትን ደረሰኝ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ለሽያጭ የቀረቡት የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች ናቸው፡፡

ስልከ ቁጥር ÷

•        011-4-40-34-34

•        ማዞሪያ 011-4-42-22-70/71/72

•        E-MAIL አድራሻ Info@dce-et.com

 

•        የድረ ገጽ አድራሻ WWW.dce-et.com

•        ፖ.ሳ.ቁ 3414 114-40-04-71/0114-42-07-46

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

Save Tender