በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር የግረዋ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የወረዳው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የ2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ኢኒስታለሽን ስራ እንዲሁም ፍርኒቸር እቃዎቸ እና ለመጋጣጠም ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በምስራቅ ሐረርጌ መስተዳድር የግረዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
W/M/A/Gurawaa-2018-002
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር የግረዋ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የወረዳው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የ2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ኢኒስታለሽን ስራ እንዲሁም ፍርኒቸር እቃዎቸ እና ለመጋጣጠም ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች ዕቃዎቹን ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ/ያደሰ መሆን አለበት፡፡
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገበ እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
4. የጨረታው ማስከበሪያ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በግረዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አሠርቶ ማቅረብ የሚቸል።
5. ተጫራቾች ከማንኛውም የሙስና ወንጀል እና ኪራይ ሰብሳቢነት ነፃ መሆን አለባቸው፡፡
6. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፋቸው ዕቃዎች በተባለበት ቦታ ማድረስ የሚችልና ያሸነፋቸው ዕቃዎች በሚፈለገው መጠን ያለው መሆን አለበት፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል በምስ/ሐ/መስ/የግረዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ16 ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
10. እቃዎች በኢትዮጵያ ማቴሪያል እስታንዳርድ የተረጋገጠ መሆን እንዳለበት ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው። በዚህ ያልተረጋገጠ እቃ ካላቀረቡ መ/ቤቱ እንደማይቀበል ማወቅ አለባቸው፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0939902153 በስራ ሰአት ደውለው ወይም በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ።
በምስራቅ ሐረርጌ መስተዳድር የግረዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
