የአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሚ ኩራ ምድብ ችሎት የፍ/ባለመብት ፋንታነሽ ገብሩ የፍ/ባለእዳ ወ/ሮ ትዕግስት አበበ መካከል ስላለው የፍ/አፈፃፀም ጉዳይ በፍርድ ባለዕዳ ተመዝግበው የሚገኘው ቶዮታ ኮሮላ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሚ ኩራ ምድብ ችሎት
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው መስፈርት
የፍ/ባለመብት ፋንታነሽ ገብሩ የፍ/ባለእዳ ወ/ሮ ትዕግስት አበበ መካከል ስላለው የፍ/አፈፃፀም ጉዳይ በፍርድ ባለዕዳ ተመዝግበው የሚገኘው ቶዮታ ኮሮላ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
1. በጨረታ የሚሸጠው መኪና ቶዮታ ኮሮላ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-A27859 አ.አ፤ የሻንሲ ቁጥር NZEI20-3050002፤ የሞተር ቁጥር 2NZ-3128727።
2. የተመረተበት ሀገር ጃፓን
3. ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 658,275.84 (ስድስት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሰባት አምስት ብር ከሰማኒያ አራት ሳንቲም)።
4. በጨረታ መግዛት የሚፈልግ ሰው በሙሉ የጨረታ ሰነድ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር ከፍሎ መግዛት ይኖርበታል፡፡
5. ተጫራቾች ለጨረታው የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር በሞዴል 85 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ሂሳብ ቁጥር ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ገንዘቡ ጨረታውን ላሸነፈው ከመኪናው ግዥ ሂሳብ ላይ የሚካተትለት ወይም የሚመለስለት ሲሆን ጨረታውን ላላሸነፉ ከጨረታው በኋላ ወዲያው ተመላሽ የሚደረግላቸው ይሆናል፡፡
6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አንድ ወር ግዜ የሚቆይ ይሆናል።
7. መኪናውን በጨረታ መግዛት የሚፈልግ አካል የጨረታ ሰነድ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ በ500 ብር ከገዛ በኋላ እንደገና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ሂሳብ ቁጥር ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር በሞደል 85 በማስገባት የሚወዳደርበትን የመኪናው ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አሽጎ ለለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርበታል።
8. የጨረታው ሰነድ የጨረታ ኮሚቴ እና ተጫራቾች ባሉበት የሚከፈት ይሆናል። ይህም በውስጥ ማስታወቂያ ከአዲስ ዘመን የጋዜጣ ማስታወቂያ በኋላ የሚነገር ይሆናል፡፡
9. የመኪናውን ይዞታ እና ሞዴል ለማወቅ የፈለገ አካል መኪናው ተይዞ ባለበት በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ማየት ይችላል፡፡
10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 251-116506205 ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ይደውሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሚ ኩራ ምድብ ችሎት
