የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት፡-
|
ተ/ቁ |
የሎት ዝርዝር |
የዕቃው አይነት |
|
1 |
ሎት 1 |
የኤክትሮኒክስ ዕቃዎች |
|
2 |
ሎት 2 |
ፑል እና ቴብልቴኒስ መጫወቻ |
|
3 |
ሎት 3 |
ፈርኒቸር |
በመሆኑም በንግድ ዘርፋ የታደሰ ፈቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
⁕ ተጫራቾች በዘርፉ ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸዉን የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ።
⁕ ተጫራቾች ለያንዳንዱ ሎቶች ለመጫረት የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 0.5% ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
⁕ ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 1ዐኛው ቀን 11፡30 ድረስ ለያነዳንዱ ሎት ብር 200 የማይመለስ በመክፈል ከቢሮው የግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሮክቶሬት ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
⁕ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ (ኘሮፎርማ) በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 11፡30 ድረስ የቴክኒካልና የፋይናሻል የመጫረቻ ሰነዶችን ኦርጅናልና አንድ አንድ ኮፒ በተለያዩ ፖሰታ በማሸግና ሲፒኦ በቴከኒካል ኦርጅናል ዶከሜንት ውስጥ በመክተትና አጠቃላዩን በአንድ ፖስታ በማሸግ በቢሮ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
⁕ የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 09፡00 ሰዓት ታሽጐ 09፡30 ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሮክቶሬት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመክፈቱ ሥነ- ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል፡፡
ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ዱራሜ አዲሱ ሉዳ ህንጻ ላይ ይገኛል
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0911565078/0916863812
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
