Tender Detail

Tender Details


ት/ቤታችን ስኩል ኦፍ ሪደምሽን አ.ማ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሥራዎች በሚያቀርበው ናሙና መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

School of Redemption (ስኩል ኦፍ ሪዴምሽን አ.ማ)


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ት/ቤታችን ስኩል ኦፍ ሪደምሽን አ.ማ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሥራዎች በሚያቀርበው ናሙና መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

1.     የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ዓመታዊ የኦዲት ሥራ

2.     የት/ቤት ወላጅ ግንኙነት መጽሐፍ

3.     የተማሪዎች የደንብ ልብስ (Uniform)

4.     የጥበቃና የጽዳት ሠራተኛ ልብስ እንዲሁም የሠራተኛ ሸሚዝ

5.     የቅድመ አንደኛ ደረጃ (KG) ተማሪዎች መመረቂያ መጽሔት

በመሆኑም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ እና የግብር ከፋይመለያ ቁጥር (Tin no.) ያላችሁ እና በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ የማይመለስ 1,000 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ለቡ ሙዚቃ ቤት በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት በመምጣት ሰነዱን በመግዛት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ጨረታው አየር ላይ በዋለበት በ8ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ9ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

 

ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ለቡ ሙዚቃ ሰፈር

ስልክ:- 0906-96-94-96/0938-11-88-22

 

ስኩል ኦፍ ሪደምሽን አ.ማ

Save Tender