ፀደይ ባንክ አ.ማ በባህርዳር ከተማ ያሉትን ሁለት ህንፃዎች ከከተማው ኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ የመብራት ማስዋብ ስራ ኤሌክትሪካል ፣ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ ወይም ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆነ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል፡፡
Tsedey Bank S.C
|
|
ፀደይ ባንክ/አ.ማ/ Tsedey Bank (S.C) | |||
| የጨረታ ማስታወቂያ | ||||
| የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/0015/2018 |
ፀደይ ባንክ አ.ማ በባህርዳር ከተማ ያሉትን ሁለት ህንፃዎች ከከተማው ኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ የመብራት ማስዋብ ስራ ኤሌክትሪካል ፣ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ ወይም ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆነ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት/ነጋዴ/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ፣ በጨረታ ለመካፈል /ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት/ክሊራንስ/ ሊኖራቸዉ ይገባል።
- ቴክኒካል ዶክመንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ዶክመንቱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ የ90ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡ ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ሰኔ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0115581658
ፀደይ ባንክ አ.ማ
