Tender Detail

Tender Details

  • Company Ghion Hotel
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline04 Jun 2026, 10:15 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-05-22 10:30:00
  • Categories Rent , Land, House, Building And Warehouse Rent

የግዮን ሆቴል ድርጅት በቅጥር ጊቢ ውስጥ የሚገኙ ለተለያዩ የንግድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሱቆችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Ghion Hotel


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዮን ሆቴል ድርጅት በቅጥር ጊቢ ውስጥ የሚገኙ ለተለያዩ የንግድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሱቆችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

የተፈቀዱ የንግድ አይነቶች

  • ለካፌ እና ለሬስቶራንት       – ለሶቬኒር ሱቆች
  • ለዲኮርና አበባ መሸጫ       – ለባህል አልባሳት መሸጫ ሱቆች
  • ለውበት ሣሎን
  • ለተለያዩ ሱቆች እና ድርጅቱ ከሚሰጠው አገልግሎት ውጭ ለሆኑ የንግድ አይነቶች

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  • ለሚሠሩት የንግድ ሥራ ኘሮፖዛል ማቅረብ፤
  • በዘርፉ ለሚሰማሩበት ሞያ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤
  • የንግድ ምዘገባ ሰርተፍኬት፤
  • የሚከራዩትን የንግድ ቤት ከተማ አስተዳደሩ በሚያወጣው ስታንዳርድ መሠረት የተጀመሩ የእድሳት ሥራውን በራሣቸው ወጪ ለማጠናቀቅ እና ለስድስት ወር ውል ለመግባት ፈቃደኛ የሆኑ፤
  • ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ጨረታ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በዋናው እንግዳ መቀበያ በመክፈል ለእያንዳንዱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከፋሲሊቲ መምሪያ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • የጨረታው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ በወጣበት በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115513222 Ext. 5429/5163 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  • የሥራ ሰዓት፡ ከሰኞ እስከ ሀሙስ ጠዋት 2፡00 – 6፡00

ከሰዓት 7፡00 – 11፡00

አርብ ጠዋት ከ2፡00 – 5፡30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡00

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የግዮን ሆቴሎች ድርጅት

Save Tender