በጉ/ክ/ከተማ አዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት የሶስተኛ ዙር ሰርቨር, EMR (Electro medical record) ከነ ዝርጋታው ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጉ/ክ/ከተማ አዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ
የሶስተኛ ዙር ዕቃ ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 003/2018 ዓ.ም
በጉ/ክ/ከተማ አዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት የሶስተኛ ዙር ሰርቨር, EMR (Electro medical record) ከነ ዝርጋታው ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ለዚህም፡-
1. ማንኛውም ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የቫት ተመዝጋቢ የሆነ የዘመኑን ግብር የከፈለና በአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገበ በራሱ ትራንስፖርት ጤና ጣቢያው ንብረት ከፍል ድረስ ማቅረብ የሚችል።
2. ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ የዕቃውን ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1 EMR/ሰርቨር ዕቃዎች 30,000 በጤና ጣቢያው ስም በሎቱ የተገለፀውን CPO(ሲፒኦ) ማቅረብ አለባቸው።
3. አሸናፊ ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ የሚውል የጠቅላላ ዋጋ 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ማንኛውም ተጫራች የዕቃዎቹን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ጤና ጣቢያው ድረስ በመምጣት አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 ግዥ ክፍል ሰነዱን መግዛት ይችላል። ሆኖም ግን በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ በዋስትና ደብዳቤ ሰነዱን በነፃ መውሰድ የሚችሉ ይሆንና ነገር ግን ድርጅታቸው በማያመርቱባቸው እቃዎች/ሎቶች ላይ የጨረታ ሰነድ የሚገዙ እና የጨረታ ማስከበሪያ CPO(ሲፒኦ) ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የጨረታ ሰነዱን የሚወዳደሩበትን ሎት ዋጋ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ/በየሎቱ ታሽጎ/ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በ10ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ በ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል። 11ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
7. የጨረታ ሰነዱን ዋጋ ሞልተው ለማስገባት ሲመጡ በቅድሚያ ናሙና መቅረብ ባለባቸው እቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበትን እቃ መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው አመቱን ሙሉ ማቅረብ የሚችል።
9. ጤና ጣቢያው የዕቃውን ብዛት እንደአስፈላጊነቱ ከውል በፊትም 20% እና ከውል በኋላ 25% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. መስሪያ ቤቱ የዕቃውን አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው እስከ 6 ወር ድረስ የእቃውን 25% በንጥል ዋጋ ተጨማሪ ግዥ ትዕዛዝ ሰጥቶ ግዥ መፈፀም ይችላል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሽሮሜዳ ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን ሳይደርሱ በስተግራ በሚያስገባው አስፓልት 500 ሜትር ገባ ብሎ በቀድሞው ቀበሌ 23/18 ባሁኑ ወረዳ 6 አጠገብ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0911899632 / ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉ/ክ/ከተማ የአዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ
