የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ታክስ ባለመክፈላቸው ምክንያት የባለዕዳዎቹን የጋራ ህንጻ ቤት በአዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀጽ 41 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሀራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ
የሀራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ታክስ ከፋዮች 1ኛ/ እነ መሀመድ ከማል እና አለባቸው ሀሰን የሚፈለግባቸውን ታክስ ብር 17,470,862.78 (አስራ ሰባት ሚሊዮን አራት መቶ ሰባ ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ ሁለት ብር ከሰባ ስምንት ሳንቲም) ስላልከፈሉ አድራሻው አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ አራዳ ክ/ከተማ 03 ቀበሌ የቤት ቁጥር 097 የሆነውን የታክስ ባለዕዳዎቹን የጋራ ህንጻ ቤት 2ኛ/ አቶ ጫኔ ኑር መሀመድ የሚፈለግባቸውን ታክስ ብር 5012.87591 (አምስት ሚሊየን አስራ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሰባ አምስት ብር ከዘጠና አንድ ሳንቲም) ስላልከፈሉ አድራሻው አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ሰኞ ገበያ ክ/ከተማ 02/06 ቀበሌ የቤት ቁጥር 097/ለ የሆነውን የታክስ ባለዕዳውን መኖሪያ ቤት የገቢዎች ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 241/2008 አንቀጽ 41 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሀራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
1. እነ መሀመድ ከማል እና አለባቸው ሀሰን የሀብቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት ብር 142,158,491.36 (አንድ መቶ አርባ ሁለት ሚሊየን አንድ መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ አራት መቶ ዘጠና አንድ ብር ከሰላሳ ስድስት ሳንቲም) ነው፡፡
2. የአቶ ጫኔ ኑርየ መሀመድ የሀብቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት ብር 9,362,033,95 (ዘጠኝ ሚሊየን ሶስት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ ሰላሳ ሶስት ብር ከዘጠና አምስት ሳንቲም) ነው፡፡
3. ስለሀብቱ አሻሻጥ መረጃ ከደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ የገቢ አወ/አሰ/ክት/ ቡድን ክፍል ማግኘት ይቻላል።
4. ተጫራቾች በቅድሚያ የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/10 ኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው።
5. ተጫራቾች ሀብቱን የሚገዙበትን ዋጋ በግልጽ በማስፈር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርገው አድራሻው ደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ በማለት አስፍረው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የግልጽ ጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ይከፈታል።
7. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከገዥው ዋጋ ጋር ታስቦ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመክፈል ሀብቱን መረከብ አለበት።
8. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ አገዥው ዋጋ ጋር ታስቦ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመክፈል ሀብቱን መረከብ አለበት፡፡
9. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆን ለጨረታው በዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ የጨረታው አሸናፈነቱ ይሠረዛል፡፡
10. ገቢዎች መምሪያው ስለሀብቶቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ሊሠርዝ ይችላል፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ
