Tender Detail

Tender Details

  • Company GLOBAL INSURANCE COMPANY (S.C)
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline30 May 2026, 10:00 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-05-30 10:30:00
  • Categories Rent , Land, House, Building And Warehouse Rent

ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ በቦሌ መንገድ ከሱር ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት ገባ ብሎ ወይም ከዲቦራ ፋውንዴሽን አጠገብ ያስገነባውን (2B+G+9) ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ

GLOBAL INSURANCE COMPANY (S.C)


ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ

የሕንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ በቦሌ መንገድ ከሱር ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት ገባ ብሎ ወይም ከዲቦራ ፋውንዴሽን አጠገብ ያስገነባውን (2B+G+9) ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ

  • ለንግድና ለቢሮ የምድር ወለል እና እስከ 2ኛ ወለል
  • ለአፓርትመንት (መኖሪያ) ከ3ኛ ወለል እስከ 9ኛ ወለል ድረስ ማከራየት ይፈልጋል

ሕንፃው የተሟላ የፓርኪንግ፣ የኤሌትሪክ ኃይል፣ የውሀ አቅርቦት እና የኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ያለው ሲሆን ለቢሮና እና ለንግድ የሚውሉ የሕንፃው ሙሉውን ወይም እንደምርጫው በከፊል ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የተጫራጮች ሕንፃው በሚገኝበት ቦታ ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ተገኝቶ በማየት ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ሱማሌ ተራ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ ማስገቢያ የተዘጋጀው ቅፅ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ያስገቡት ሰነድ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን በጨረታው ላይ ለመገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት መገኘት ይችላሉ፡፡
  3. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥሮች 0111 56 74 00/ 0111 56 58 50 /0111 56 58 53 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

Save Tender

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለአዳማ-አሰላ፣ ጨፌ ዶንሳ ፤ለአዲስ አበባ እና ሃረር መንገድ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በዚህ ዘር...

READ MORE
የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች (ባጃጅ ተራ፣ ጂ፣ ኤች እና አይ ፓርኪንግ) ኪራይ ጨረታ - የቂርቆስ ገበያ ማዕከል አ/ማ

READ MORE