Tender Detail

Tender Details

  • Company የምስራቅ የምግብ ማቀነባበሪያ ኃላ/የተ/ የግል ማህበር
  • Address ጎተራ ማሳለጫ አካባቢ ከያሬድ ቤተ-ክርስቲያን በስተጀርባ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-86-22-22-00
  • Website
  • Deadline25 May 2026, 4:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityለሎት 1 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለሎት 2 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) እና ለሎት 3 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
  • opening date2026-05-25 04:30:00
  • Categories Materials , Used Items , Vehicle

ድርጅታችን ምሥራቅ የምግብ ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማ ልዩ ልዩ ያገለገሉ የጭነት ተሽከርካሪዎችን፣ ባዶ ካርቶኖችን እና የፒፒ ከረጢቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የምስራቅ የምግብ ማቀነባበሪያ ኃላ/የተ/ የግል ማህበር


ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሸያጭ

ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2018

 

ድርጅታችን ምሥራቅ የምግብ ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማ ልዩ ልዩ ያገለገሉ የጭነት ተሽከርካሪዎችን፣ ባዶ ካርቶኖችን እና የፒፒ ከረጢቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት እነዚህን ዕቃዎች ተጫርቶ መግዛት ይችላል።

ሎት 1 ያገለገሉ ልዩ ልዩ የጭነት ተሽከርካሪዎች

ሎት 2 ያገለገሉ ልዩ ልዩ የኤሌክትሪክ ሞተሮች

ሎት 2 የተለያዩ ባዶ ካርቶኖች እና የፒፒ ከረጢቶች

1.     በዚህ ጨረታ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።

2.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 አንዲሁም ቅዳሜ እስከ 6፡00 መውሰድ ይችላሉ።

3.     የዕቃዎች ሽያጭ የሚከናወነው ባሉበት ሁኔታ መሠረት ይሆናል።

4.     በሎት 1 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5.     በሎት 2 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

በሎት 3 የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) ወይም በባንከ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6.     ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ የያዘ የጨረታ ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

ጨረታው በመጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል። 10ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በተከታዩ ቀን ይከፈታል።

7.     ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0953480200/ 0907881291 ወይም ጎተራ ማሳለጫ አካባቢ ያሬድ ቤተክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።

 

ምሥራቅ የምግብ ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማ

Save Tender