የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ቋሚ ምድብ ችሎት የአፈጻጸም ክርክርን አስመልክቶ የፍርድ ባለ እዳ የሆኑት ንብረት የሆነውን WHEEL LOODER ማሽን በጨረታ ለመሸጥ ስለሚፈልግ ይህን መኖሪያ ቤት በጨረታ ለመግዛት የሚፈልጉ ሰዎች ወይም አካላት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት
2ኛ ግዜ የጨረታ ማስታወቂያ
የፍርድ ባለ መብት የቢሾፍቱ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና የፍርድ ባለ እዳ ጳውሎስ ዘለቀ ጠቅላላ ተቋራጭ የግንባታ ድርጅት መካከል ያለውን የውሳኔ አፈጻጸም ክርክርን አስመልክቶ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ቋሚ ምድብ ችሎት የፍርድ ባለ እዳ የሆኑት ንብረት WHEEL LOODER ማሽን ሞዴሉ CLG 855 የሻንስ ቁጥሩ FT0800597, የሞተር ቁጥር 1508B030339 የሆነ የመነሻ ዋጋ ብር 4,500,000.00 (አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ) በሆነው በ06/10/2018 ከጠዋቱ 3፡00 አንስቶ እስከ 6፡00 መካከል ግልጽ ጨረታ በማካሄድ በሚገኘው ከፍተኛ ዋጋ ተሸጦ የጨረታው ውጤት በሰኔ ቀን 10/10/2018 ከሰአት በፊት 4፡00 ሰዓት እንዲቀርብ ታዟል።
ይህ ማስታወቂያ ከግንቦት 04/09/2018 በፊት ታትሞ እስከ ሰኔ 5/10/2018 በአየር ላይ እንዲቆይ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት አዟል።
ከላይ የተጠቀሱትን WHEE LOODER ማሽን በጨረታው ላይ በመወዳደር መግዛት የምትፈልጉ
1. የጨረታውን መነሻ ዋጋ ለጨረታ ተገልጾ የቀረበውን ንብረት 1/4ኛውን እጅ በሲንቄ ባንክ CPO በማስያዝ ቀርበው መመዝገብ ይችላሉ፡፡
2. ለመመዝገብ ሲመጡ መታወቅያ ወረቀት በመያዝ መቅረብ አለባቸው፡፡
3. የጨረታን ውድድር ያሸነፈንፉ ሰው/ ሰዎች የሚቀረውን ገንዘብ ችሎቱ በሚሰጥበት ቀን ውስጥ አጠናቆ የሚያስገባ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉ ሰዎች ያስያዙት ማስረጃ ወድያውኑ የሚመለስላቸው ይሆናል።
4. ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በላንድ ፊል ግቢ ወይም ጋረ በሩ በሚባልበት ከላይ በተገለጸው ቀን እና ሰአት የሚከፈት ይሆናል፡፡
5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በአለቻ ኦሮሚያ ጋዜጣ እንዲታተም ታዟል።
ለተጨማሪ ሃሳብ በተለየ ሁኔታ በፍርድ ባለ መብት አቶ ተስፋዬ ቱፋ በእጅ ስልክ 09 74 50 18 08 እና በፍርድ ባለ እዳ አቶ ጳውሎስ ዘለቀ በእጅ ስልክ 09 12 88 77 88 በሆነው ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ሄዳችሁ ማየት ትችላላችሁ፡፡
በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምስራቅ ኦሮሚያ ቋሚ ምድብ ችሎት የፍታብሔር ጉዳይ
