በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት ለጂ/ከ/አስተዳደር ለሴክተር መ/ቤቶች የኤሌክትሮኒክስ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች እና የማዘጋጃ ቤት የማሽነሪ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
በአሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት ለጂ/ከ/አስተዳደር ለሴክተር መ/ቤቶች የኤሌክትሮኒክስ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች እና የማዘጋጃ ቤት የማሽነሪ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
1. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዋች C.P.O - 10,000 /አስር ሺህ ብር/
2. የመኪና መለዋወጫ C.P.O - 10,000 /አስር ሺህ ብር/
3. የማሽን መለዋወጫ ዕቃ C.P.O - 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/
በዚህም መስረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡- በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ እና የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የጂ/ከ/አስ/ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት የግዥ ስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የንግድ ፍቃድ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት፣ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሰነዱን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ በጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ጽ/ቤት ስም ከታወቀ ወይም ስልጣን ከተሰጠው አካል የጨረታ ማስከበሪያ በማዘጋጀት ከጨረታው ዶክመንት ጋር በማስገባት ማስያዝ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ኦርጅናል ዶክመንታቸውን ይዘው መቅረብ አለባቸው አሸናፊው ተጫራቾች ያሸነፉባቸው ስራ ለመፈፀም ያሸነፈበት ገንዘብ 10 % ስያሲዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ወይም ቀኑ በስራ ቀን ካልዋለ በማግስቱ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት በ4፡30 ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ጨረታ በሚከፍትበት ወቅት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አይስተጓጎልም፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0467750256 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኣሪ ዞን የጂንካ ከተማ /ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት
